እነዚህ ደግሞ የቡዝ ልጅ፣ የዬዳይ ልጅ፣ የኢዬሳይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የኢዳይ ልጅ፣ የዑሪ ልጅ፣ የሑሪ ልጅ፣ የአቢካኢል ልጆች ናቸው።
ቤተ ዘመዶቻቸውም በየቤተ ሰቡ እነዚህ ነበሩ፤ ሚካኤል፣ ሜሱላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዙኤ፣ ኦቤድ፤ በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ።
የቤተ ሰባቸውም አለቃ የጉኒ ልጅ፣ የአብዲኤል ልጅ አሒ ነበረ።