አለቃው ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ሳፋም ከዚያም ያናይና ሰፋጥ ሆነው በባሳን ተቀመጡ።
የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤
ቤተ ዘመዶቻቸውም በየቤተ ሰቡ እነዚህ ነበሩ፤ ሚካኤል፣ ሜሱላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዙኤ፣ ኦቤድ፤ በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ።