በአካባቢያቸው የሚገኙት መንደሮች ደግሞ ኤጣም፣ ዓይን፣ ሬሞን፣ ቶኬን፣ ዓሻን የተባሉ ዐምስት ከተሞች ናቸው፤
ቤትማርካቦት፣ ሐጸርሱሲም፣ ቤት ቢሪ፣ ሽዓራይም፤ እስከ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ድረስ የኖሩት በእነዚህ ከተሞች ነው።
በእነዚህም ከተሞች ዙሪያ እስከ ባኣል የሚዘልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን። የትውልድ መዝገብም አላቸው።
ዓይን፣ ሪሞን፣ ዔቴርና ዓሻን የተባሉት አራት ከተሞቻቸውና መንደሮቻቸው፣
ዓይንን፣ ዩጣንና ቤትሳሚስን ከነመሰማሪያቸው ሰጧቸው፤ እነዚህ ዘጠኙ ከተሞች ከሁሉ ነገዶች ይዞታ ላይ ተከፍለው የተሰጡ ናቸው።