ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው።
የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤ የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጐሣዎች አባት ለዓዳ፣
ሰዎቹ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።