የይሃሌልኤል ወንዶች ልጆች፤ ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣ አሣርኤል።
የዮፎኒ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም። የኤላ ልጅ፤ ቄኔዝ።
የዕዝራ ወንዶች ልጆች፤ ዬቴር፣ ሜሬድ፣ ዔፌር፣ ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች አንዲቱ ማርያምን፣ ሸማይንና የኤሽትሞዓን አባት ይሽባን ወለደች።
ከዚያም እነዚሁ ሌዋውያን በሥራው ላይ ተሰማሩ፤ ከቀዓት ዘሮች የአማሢ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፤ ከሜራሪ ዘሮች፣ የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፤ ከጌርሶን ዘሮች፣ የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ዔድን፤