የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ ጎቶንያል፣ ሠራያ። የጎቶንያል ወንዶች ልጆች፤ ሐታት፣ መዖኖታይ።
ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን፣ የዒርናሐሽን ከተሞች የቈረቈረውን ተሒናን ወለደ። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።
መዖኖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ። ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው።
ስለዚህ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዛት፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት።
በዚህ ጊዜ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳንን ዳረለት።