የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ።
ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋራ ትሁን፤ ከሥቃይና ከጕዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን፣ የዒርናሐሽን ከተሞች የቈረቈረውን ተሒናን ወለደ። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።