ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።
ዳዊት ከኬብሮን ከሄደ በኋላ፣ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤ ቁባቶችንም አስቀመጠ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።
እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ የሮብዓም ልጅ አብያ፣ የአብያ ልጅ አሳ፣ የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣
ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላሉ፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።