ዐምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያ፣ ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።
አራተኛው፣ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፤ ዐምስተኛው፣ ከአቢጣል የተወለደው ሰፋጥያ፣
ስድስተኛው፣ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም ነበር። እነዚህ ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ናቸው።
ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣ አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣
እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር። ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤