የሴኬንያ ዘሮች፤ ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ ሐጡስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፤ በአጠቃላይ ስድስት ነበሩ።
የሐናንያ ዘሮች፤ ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች።
የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤ ኤልዮዔናይ፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዝሪቃም፤ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ።
ከፊንሐስ ዘሮች ጌርሶን፤ ከኢታምር ዘሮች ዳንኤል፤ ከዳዊት ዘሮች ሐጡስ፤
እርሱም ከሴኬንያ ዘሮች ነው፤ ከፋሮስ ዘሮች ዘካርያስና ከርሱም ጋራ 150 ወንዶች ተመዝግበው ነበር፤