ሌሎችም ዐምስት ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ።
የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤ ዘሩባቤል፣ ሰሜኢ። የዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፤ ሜሱላም፣ ሐናንያ፤ እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች።
የሐናንያ ዘሮች፤ ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች።