የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፤ ልጁ ሰላትያል፣
የኢዮአቄም ዘሮች፤ ልጁ ኢኮንያ፣ ልጁ ሴዴቅያስ።
መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።
ከዚያም የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱና ካህናት ዘመዶቹ እንዲሁም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የሥራ ባልደረቦቹ፣ በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ፣ የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ መሥራት ጀመሩ።
ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር፣ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ እንዲሁም የቀሩት ወንድሞቻቸው (ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት ሁሉ) ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤት ሕንጻ ሥራ እንዲቈጣጠሩ ሾሟቸው፤ ሥራውንም ጀመሩ።
ከዚያም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራት ተነሡ፤ የሚያግዟቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ዐብረዋቸው ነበሩ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣ አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤ በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣ መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”
ከባቢሎን ምርኮ በኋላ፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤