ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሰጡትም ዐምስት ሺሕ መክሊት ወርቅ፣ ዐሥር ሺሕ ዳሪክ ወርቅ፣ ዐሥር ሺሕ መክሊት ብር፣ ዐሥራ ስምንት ሺሕ መክሊት ናስ አንድ መቶ ሺሕ መክሊት ብረት ነው።
ለቅጥር በሮቹ ምስማርና ማጠፊያ የሚሆን ብዙ ብረትና ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስ አዘጋጀ።
እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 5,000 ምናን ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
እያንዳንዱ የብር ሳሕን መቶ ሠላሳ ሰቅል፣ እያንዳንዱም ጐድጓዳ ሳሕን ሰባ ሰቅል፣ በአጠቃላይም የብር ሳሕኖቹ ክብደት በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺሕ አራት መቶ ሰቅል ይመዝን ነበር።
ሒሳቡን ማጣራት እንደ ጀመረም ዐሥር ሺሕ ታላንት ዕዳ ያለበትን አንድ አገልጋይ አቀረቡለት።