በሦስተኛውም ወር፣ የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፣ በሥሩ ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
የዮዳሄ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አዛዥ ነበር፤ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች ነበሩ።
ንጉሡም በኢዮአብ ቦታ የዮዳሄን ልጅ በናያስን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ በአብያታርም ቦታ ካህኑን ሳዶቅን ተካ።
ወጣቱ ብርቱ ተዋጊ ሳዶቅና ከቤተ ሰቡ ሃያ ሁለት የጦር አለቆች፤
የዮዳሄ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አዛዥ ነበር፤ የዳዊት ወንዶች ልጆቹ ደግሞ ከንጉሡ ቀጥሎ የበላይ ሹማምት ነበሩ።
የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እግር ተተኩ። ኢዮአብም የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።
በሁለተኛው ወር፣ የክፍለ ጦሩ የበላይ አዛዥ አሆሃዊው ዱዲ ሲሆን፣ የዚሁ ክፍል መሪ ደግሞ ሚቅሎት ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
ይህም በናያስ ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኀያል ሲሆን፣ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዓሚዛ ባድም የክፍሉ ሰራዊት አዛዥ ነበረ።