አስተዋይ የሆነው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሓፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሡ ልጆች ሞግዚት ነበረ።
አምኖን ኢዮናዳብ የተባለ ወዳጅ ነበረው፤ እርሱም የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ነው። ኢዮናዳብ እጅግ ተንኰለኛ ሰው ነበር።
እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ፣ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።
የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም ይህ ነው፤ ሐክሞናዊው ያሾብዓም የጦር መኰንኖቹ አለቃ ነበረ፤ እርሱም ጦሩን አንሥቶ በአንድ ጊዜ ሦስት መቶ ሰው ገደለ።
እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።
አጋራዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኀላፊ ነበረ። እነዚህ ሁሉ የንጉሥ ዳዊት ንብረት ኀላፊዎች ነበሩ።
አኪጦፌል የንጉሡ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ።