በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤ በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።
የእሴይ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሳምዓ፣
በሌዊ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የቀሙኤል ልጅ ሐሸብያ፤ በአሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ።
በዛብሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብድዩ ልጅ ይሽማያ፤ በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ለኢያሪሙት።
እዚያ በደረሱ ጊዜም፣ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፣ “በርግጥ እግዚአብሔር የቀባው ሰው እነሆ፤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል” ብሎ ዐሰበ።
ሦስቱ የእሴይ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር፤ እነርሱም ታላቁ ኤልያብ፣ ሁለተኛው አሚናዳብ፣ ሦስተኛውም ሣማ ይባላሉ፤
ዳዊትም፣ “ታዲያ ምን አደረግሁ? መጠየቅ እንኳ አልችልም?” አለ።