የሸማያ ወንዶች ልጆች፤ ዖትኒ፣ ራፋኤል፣ ዖቤድ፣ ኤልዛባድ፤ ዘመዶቹ ኤሊሁና ሰማክያም እንደዚሁ በቂ ችሎታ ነበራቸው።
እንዲሁም ልጁ ሸማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በቂ ችሎታ ስለ ነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎች ሆነው ነበር።
እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ዘሮች ሲሆኑ፣ እነርሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ቤተ ዘመዶቻቸው ሥራውን ለመሥራት በቂ ችሎታ ነበራቸው። የዖቤድኤዶም ዘሮች በአጠቃላይ ስድሳ ሁለት ነበሩ።
የቆሬ ልጅ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ ሰሎምና ከርሱም ቤተ ሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣ እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።