ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ዘካርያስ፣ ሁለተኛው ይዲኤል፣ ሦስተኛው ዝባድያ፣ አራተኛው የትኒኤል፣
የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች አመዳደብ፤ ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም።
ዐምስተኛው ኤላም፣ ስድስተኛው ይሆሐናን፣ ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።
ወደ መገናኛው ድንኳን የሚያስገባውን በር የሚጠብቀው ደግሞ የሜሱላም ልጅ ዘካርያስ ነበረ።