የደቡቡ በር ዕጣ ለአቢዳራ ሲወጣ፣ የግምጃ ቤቱ ዕጣ ደግሞ ለልጆቹ ወጣ።
የምሥራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ። ከዚያም ምክር ዐዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው።
የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ። በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ጥበቃ ነበረ፤
በየቀኑም በምሥራቅ በኩል ስድስት፣ በሰሜን በኩል አራት፣ በደቡብ በኩል አራት፣ በዕቃ ቤቱ በኩል በአንድ ጊዜ ሁለት ሌዋውያን ይጠብቁ ነበር።
እርሱም በአቢዳራ ጥበቃ ሥር የነበረውንና በአምላክ ቤተ መቅደስ የተገኘውን ወርቅ፣ ጥሬ ብርና ዕቃ በሙሉ፣ ከቤተ መንግሥቱም ንብረትና በመያዣ ከያዛቸው ሰዎች ጭምር ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ።
በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ።