ከሜራሪ ወገን የሆነው ሖሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽምሪ ነበረ፤ የበኵር ልጅ ባይሆንም እንኳ፣ አባቱ ቀዳሚ አድርጎት ነበር።
እንዲሁም ዖቤድኤዶምና ስድሳ ስምንቱ የሥራ ባልደረቦቹ ዐብረዋቸው እንዲያገለግሉ በዚያው ተዋቸው። የኤዶታም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ሆኑ።
ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ጥበልያ፣ አራተኛው ዘካርያስ፤ የሖሳ ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶቹ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
ሜሱላም በቂ ችሎታ ያላቸው ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶች ነበሩት፤ ቍጥራቸውም በአጠቃላይ ዐሥራ ስምንት ነበረ።