ከይስዓራውያን ወገን፣ ሰሎሚት፤ ከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፣ ያሐት።
የይስዓር ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሰሎሚት ነበረ።
ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤ አለቃው ይሺያ።
የኬብሮን ወንዶች ልጆች፣ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም።
ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተ ሰቡ ኀላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዛዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች ነበሩ።
የእንበረም ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ፣ ማርያም። የአሮን ወንዶች ልጆች፤ ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር።
የይስዓር ወንዶች ልጆች፣ ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ።
የቀዓት ጐሣዎች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።
የእንበረማውያን፣ የይስዓራውያን፣ የኬብሮናውያንና የዑዝኤላውያን ጐሣዎች ከቀዓት ወገን ናቸው፤ እነዚህ የቀዓት ጐሣዎች ነበሩ።