እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።
የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ለኢያሪሙት በአጠቃላይ ሦስት ናቸው።
ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቈጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።
ዕድሜያቸው ሠላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺሕ ነበረ።
በትውልድ መዝገብ በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ለገቡት ካህናት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ሌዋውያን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው አካፈሏቸው።
ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር፣ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ እንዲሁም የቀሩት ወንድሞቻቸው (ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት ሁሉ) ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤት ሕንጻ ሥራ እንዲቈጣጠሩ ሾሟቸው፤ ሥራውንም ጀመሩ።
ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ።
ከዚያም በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበረ ሰቡን በሙሉ በአንድነት ሰበሰቧቸው። የተሰበሰቡትም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረጋቸውን ተናገሩ፤
ከስምዖን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
ከዚህ በኋላ ማደሪያው ተነቀለ፤ ድንኳኑን የተሸከሙት ጌርሶናውያንና ሜራሪያውያንም ጕዞ ጀመሩ።
ከዚህ በኋላ ቀዓታውያን ንዋያተ ቅድሳቱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ከመድረሳቸው በፊት ማደሪያው ተተክሎ ነበር።
“በእስራኤላውያን ላይ ዳግም ቍጣ እንዳይደርስባቸው የመቅደሱና የመሠዊያው እንክብካቤ ኀላፊነት የሚመለከተው እናንተን ይሆናል።
በየቤተ ሰባቸው፣ በየምድባቸውና በየሰራዊታቸው የተመዘገቡት እስራኤላውያን ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ናቸው፤
“ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው።
የሜራሪ ጐሣዎች፤ ሞሖሊና ሙሲ። እንግዲህ የሌዋውያን ጐሣዎች በየቤተ ሰባቸው ሲቈጠሩ እነዚህ ናቸው።
ለእያንዳንዱ በኵር ክብደቱ ባለሃያ አቦሊ በሆነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ልክ ዐምስት ዐምስት ሰቅል ተቀበል፤
ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት የሆናቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ወንዶች ሁሉ ቍጠር።
እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቍጠሩ።
“ሌዋውያንን የሚመለከተው ደንብ ይህ ነው፤ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ለመሳተፍ ሃያ ዐምስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች ይመጣሉ፤