የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።
የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።
የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ሙሲ። የሞሖሊ ወንዶች ልጆች፤ አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።
የዑዝኤል ልጅ፣ ሚካ ከሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር።
የሚካ ወንድም ይሺያ፤ ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።
የኦዚ ወንድ ልጅ፤ ይዝረሕያ። የይዝረሕያ ወንዶች ልጆች፤ ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤል፣ ይሺያ፤ ዐምስቱም አለቆች ነበሩ።