የአልዓዛር ዘሮች፤ የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ። አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የረዓብያ ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።
የጌርሳም ዘሮች፤ ሱባኤል።
የይስዓር ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሰሎሚት ነበረ።
ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤ አለቃው ይሺያ።
የሙሴ ልጅ የጌርሳም ዘር የሆነው ሱባኤል የግምጃ ቤቱ የበላይ ኀላፊ ነበረ።
በአልዓዛር በኩል የሚዛመዱት፤ ልጁ ረዓብያ፣ ልጁ የሻያ፣ ልጁ ኢዮራም፣ ልጁ ዝክሪ፣ ልጁ ሰሎሚት።
“የአባቴ አምላክ ረዳቴ ነው፤ ከፈርዖን ሰይፍ አድኖኛልና” ለማለት ደግሞ ሁለተኛውን ልጁን አልዓዛር አለው።