የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤ ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፤ እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ናቸው።
የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ ነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቈጠሩት በሥራ መደብ እንደ አንድ ቤተ ሰብ ሆነው ነው።
የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤ ሰሎሚት፣ ሐዝኤል፣ ሐራን፤ በአጠቃላይ ሦስት ናቸው። እነዚህ የለአዳን ቤተ ሰብ አለቆች ናቸው።
የሌዊ ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የሰሜኢ ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣