ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቍጥር ለዳዊት አቀረበ፤ እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺሕ ሲሆኑ፣ ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ።
ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ።
ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል ኢዮአብን አሸነፈው፤ ስለዚህ ኢዮአብ ወጣ፤ በመላው እስራኤል ከተዘዋወረ በኋላ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛቸው ተስፋ ሰጥቶ ስለ ነበር፣ ዳዊት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በታች የሆነውን አልቈጠረም ነበር።
የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቍጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም።