ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት፣ የእግዚአብሔር መልአክ በሰማይና በምድር መካከል ቆሞ አየ፤ መልአኩም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ከዚያም ዳዊትና ሽማግሌዎቹ ማቅ እንደ ለበሱ በግምባራቸው ተደፉ።
ሰውንም ካስወጣው በኋላ፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ ከዔድን በስተምሥራቅ አኖረ።
አክዓብም ይህን ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶ፤ ጾመ፤ በማቅ ላይ ተኛ በሐዘን ኵርምት ብሎም ይሄድ ነበር።
ንጉሡ ሕዝቅያስ ይህን ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለበሰ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ገባ።
ኤልሳዕም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ያይ ዘንድ እባክህ ዐይኖቹን ክፈትለት” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የአገልጋዩን ዐይኖች ከፈተለት፤ ሲመለከትም፤ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንድ ግን ይዝላል፤ ሰይፌን በባቢሎን ንጉሥ እጅ ሳስይዝ፣ እርሱም ሲነቀንቀው፣ ያኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።
እነርሱ እየገደሉ እኔም ብቻዬን ሳለሁ፣ በግንባሬ ተደፍቼ፣ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በኢየሩሳሌም ላይ መዓትህን አውርደህ የእስራኤልን ቅሬታዎች ሁሉ ልታጠፋ ነውን?” በማለት ጮኽሁ።
ከዚያም ሙሴና አሮን እዚያ በተሰበሰቡት በመላው እስራኤላውያን ማኅበር ፊት በግንባራቸው ተደፉ።
ሙሴና አሮን ግን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንድ ሰው ኀጢአት በሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?” ሲሉ ጮኹ።
አህያዪቱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ በመንገድ ላይ መቆሙን ባየች ጊዜ ከመንገድ ወጥታ ዕርሻ ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገዱ እንድትመለስ መታት።
በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የበለዓምን ዐይን ከፈተ፤ እርሱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ እንደ ያዘ መንገዱ ላይ ቆሞ አየ፤ ጐንበስ ብሎም በግንባሩ ተደፋ።
ይኸውም የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።