ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ ‘በል እንግዲህ አንዱን ምረጥ፤
“ሂድና ዳዊትን እንዲህ ብለው ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ እነሆ፣ ሦስት ምርጫ ሰጥቼሃለሁ፤ በአንተ ላይ አደርግብህ ዘንድ አንዱን ምረጥ።’ ”
የሦስት ዓመት ራብ ወይስ የጠላቶችህ ሰይፍ ለሦስት ወር አይሎብህ መጥፋት ወይስ ሦስት ቀን የእግዚአብሔር ሰይፍ መቅሠፍት በምድሪቱ ላይ ወርዶ የእግዚአብሔር መልአክ እስራኤልን ሁሉ ያጥፋ?’ ለላከኝ ምን እንደምመልስ ወስን።”
ምክርን ስማ፤ ተግሣጽን ተቀበል፤ በመጨረሻም ጠቢብ ትሆናለህ።