የዛራ ወንዶች ልጆች፤ ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፤ በአጠቃላይ ዐምስት ናቸው።
እርሱም ከማንም ሰው ይልቅ ጥበበኛ ነበር፣ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታን፣ ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ደግሞም ከደራል ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት አሕዛብ ሁሉ ተሰማ።
ሰሎሞን ደግሞ ለኪራም ቤተ ሰብ ቀለብ እንዲሆን ሃያ ሺሕ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፣ ሃያ ሺሕ ኮር ንጹሕ የወይራ ዘይት ሰጠው፤ ይህን ባለማቋረጥ በየዓመቱ ለኪራም ይሰጥ ነበር።
የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ ኤስሮም፣ ሐሙል።
የከርሚ ወንድ ልጅ አካን፤ እርሱም ዕርም የሆነ ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።
አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ።
እስራኤላውያን ግን ዕርም የሆነውን ነገር ለራሳቸው በመውሰድ በደሉ፤ ይህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው አካን የከርሚ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የዛራ ልጅ ዕርም ከሆነው ነገር ስለ ወሰደ የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።