Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ዜና መዋዕል 2:42

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ሞሳ ሲሆን፣ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪሳም ኬብሮንን ወለደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ ኀይሌና የጕብዝናዬም መጀመሪያ፤ በክብር ትልቃለህ፤ በኀይልም ትበልጣለህ።

ሰሎም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።

የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ ቆሬ፣ ተፉዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።

ሸማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤትጹርን ወለደ።

እንዲሁም የማድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።

የቂርያትይዓይሪም አባት የሦባል ዘሮች፤ የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤

የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤ ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።

የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ። የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።

እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወሰናቸው፤ ይኸውም ከብዙ ወንድሞች መካከል እርሱ በኵር እንዲሆን ነው።

ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈው ወደ በኵራት ማኅበር ቀርባችኋል፤ የሁሉ ዳኛ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር፣ ፍጹምነትን ወዳገኙት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፣

ዚፍ፣ ጤሌም፣ በዓሎት፣

ቅዒላ፣ አክዚብና መሪሳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዘጠኝ ናቸው።

ማዖን፣ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣ ዩጣ

የዚፍ ሰዎች ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል ወጥተው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ ዳዊት ከየሴሞን በስተ ደቡብ በኤኬላ ኰረብታ ላይ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቆ የለምን?

የዚፍ ሰዎች ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ መጥተው፣ “እነሆ፤ ዳዊት በየሴሞን ትይዩ በሚገኘው በኤኬላ ኰረብታ ተደብቋል” ብለው ነገሩት።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች