ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ያስተዳድር ነበር።
ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።
ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ስድሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።
ስለዚህ ሙሴ ገለዓድን የምናሴ ዘሮች ለሆኑት ለማኪራውያን ሰጣቸው፤ እነርሱም መኖሪያቸውን በዚያው አደረጉ።
ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር መኖሪያቸውን ወስዶ፣ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው።
ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር፣ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ወሰን ድረስ የሚገኘውን መላውን የአርጎብ ምድር ወሰደ፤ ምድሪቱም በስሙ ተጠራች፤ ከዚሁ የተነሣ ባሳን እስከ ዛሬ ድረስ ሓቦት ኢያዕር ትባላለች።
ገለዓድንም ለማኪር ሰጠሁት።
ድንበራቸው ከመሃናይም አንሥቶ ባሳንን በሙሉ ይጨምርና፣ በባሳን ያሉትን ስድሳ የኢያዕር ከተሞች ሁሉ ይዞ የባሳን ንጉሥ የዐግን ግዛት ሁሉ የሚያካትት ሲሆን፣