አራም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤
ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ።
የኤስሮም ወንዶች ልጆች፤ ይረሕምኤል፣ አራም፣ ካሌብ።
አሮንም የአሚናዳብን ልጅ፣ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።
ከይሁዳ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፤
በመጀመሪያ የይሁዳ ሰፈር ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ሆነው ተጓዙ፤ አለቃቸውም የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር።
በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ፤ የይሁዳ ምድብ፤ በየሰራዊቱና በዐርማቸው ሥር ይስፈር፤ የይሁዳ ሕዝብ አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው፤
በመጀመሪያው ቀን ስጦታውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፤
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።
አራም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤