ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ወደ ፊት በመገሥገሥም ከፊት ለፊታቸው የውጊያ መሥመሩን ያዘ። ዳዊትም ሶርያውያንን ጦርነት ለመግጠም ወታደሮቹን አሰለፈ፤ እነርሱም ተዋጉት።
ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ መላውን እስራኤልን ሰብስቦ፤ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ኤላም ሄደ።
ሶርያውያን በእስራኤላውያን እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ፣ መልእክተኞችን ልከው ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ያሉትን ሶርያውያን አስመጡ፤ እነዚህንም የሚመራቸው የአድርአዛር ሰራዊት አዛዥ ሾፋክ ነበረ።
ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ። ዳዊትም ሰባት ሺሕ ሠረገለኞችና አርባ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ገደለ። የሰራዊታቸው አዛዥ ሾፋክም በጦርነቱ ላይ ሞተ።
አሞናውያንም መጥተው ወደ ከተማቸው በሚያስገባው በር ላይ ለጦርነት ተሰለፉ፤ የመጡት ነገሥታት ደግሞ ብቻቸውን በሜዳው ላይ ነበሩ።