እግዚአብሔርንና ብርታቱን ፈልጉ፤ ፊቱንም ዘወትር ፈልጉ።
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ።
“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ተነሥ፣ ከኀይልህ ታቦት ጋራ ወደ ማረፊያ ቦታህ ግባ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ካህናትህ ድነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በቸርነትህ ደስ ይበላቸው።
እርሱን የሚፈልግ ትውልድ እንዲህ ነው፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ፊትህን የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው። ሴላ
ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል?” ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።
እግዚአብሔር ይማረን፤ ይባርከን፤ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ ሴላ
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኀይልና ብርታትን ይሰጣል። እግዚአብሔር ይባረክ!
የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።
በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣ የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል፤ የበልጕም ዝናብ ያረሰርሰዋል።
እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ አለዚያ እንደ እሳት የዮሴፍን ቤት ያወድማል፤ እሳቱም ቤቴልን ይበላል፤ የሚያጠፋውም የለም።