ከኬብሮን ዘሮች፣ አለቃውን ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
ከዑዝኤል ዘሮች፣ አለቃውን አሚናዳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።
ከኤሊጻፋን ዘሮች፣ አለቃውን ሸማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤
የቀዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው።
የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።
ከእንበረማውያን፣ ከይስዓራውያን፣ ከኬብሮናውያን፣ ከዑዝኤላውያን፤
የቀዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።
የቀዓት ወንዶች ልጆች እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፤ ቀዓት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ኖረ።
እነዚህም ደግሞ የሌዊ ጐሣዎች ነበሩ፤ የሊብናውያን ጐሣ፣ የኬብሮናውያን ጐሣ፣ የሞሖላውያን ጐሣ፣ የሙሳውያን ጐሣ፣ የቆሬያውያን ጐሣ። ቀዓት የእንበረም አባት ነበረ፤