ከጌርሶን ዘሮች፣ አለቃውን ኢዩኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤
ከዚያም ዳዊት ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፣ ሌዋውያኑን ኡርኤልን፣ ዓሣያን፣ ኢዩኤልን፣ ሸማያን፣ ኤሊኤልንና አሚናዳብን ጠርቶ፣
ከሜራሪ ዘሮች፣ አለቃውን ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
ከኤሊጻፋን ዘሮች፣ አለቃውን ሸማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤
የለአዳን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዩኤል፤ በአጠቃላይ ሦስት ናቸው።