የጦር መሣሪያውን በአማልክታቸው ቤተ ጣዖት አስቀመጡት፤ ራሱንም በዳጎን ቤተ ጣዖት ውስጥ አንጠለጠሉት።
የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ፣
ሳኦልን ከገፈፉ፣ ራሱን ከቈረጡና መሣሪያውንም ከወሰዱ በኋላ፣ ለጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲናገሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክተኞችን ላኩ።
የጦር መሣሪያውን በአስታሮት ቤተ ጣዖት ውስጥ አስቀመጡት፤ ሬሳውን ደግሞ በቤትሳን ግንብ ላይ አንጠለጠሉት።