የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሜሼኽ፣ ቴራስ።
የኖኅ ወንዶች ልጆች፤ ሴም፣ ካም፣ ያፌት።
የጎሜር ልጆች፤ አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቶጋርማ።
በሜሼኽ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ!
“ ‘ያዋን፣ ቶቤልና ሜሼኽ ከአንቺ ጋራ ይነግዱ ነበር፤ ባሪያዎችንና የናስ ዕቃዎችን በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።
ደግሞም ጎሜርን ከወታደሮቹ ጋራ፣ ራቅ ካለው ሰሜንም የቶጋርማን ቤት ከወታደሮቹ ሁሉ ጋራ ብዙ ሕዝቦችን ከአንተ ጋራ አስወጣለሁ።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ፤ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የሜሼኽና የቶቤል ዋና አለቃ ጎግ ሆይ፤ ተነሥቼብሃለሁ፤