አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ።
የሴም ልጆች፤ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው። የአራም ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሜሼኽ።
ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፋሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።