Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


98 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ለወላጆች መታዘዝ

98 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ለወላጆች መታዘዝ

ልጆችም ሆኑ ወጣቶች፣ አልፎ ተርፎም አዋቂዎች፣ በጊዜ ሂደት ወላጆቻችንን ማክበርና መታዘዝ እንድንማር የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን አስተውል። ይህን ማድረግ በጥበብ እንድንኖር ይረዳናል።

«እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ» ይላል (ዘዳግም 5:16)።

ወንጌልን ስናነብ፣ ኢየሱስ ገና በወጣትነቱ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ሳለ እንኳን ለምድራዊ ወላጆቹ እንደታዘዘና በጥበብ እንደ አደገ በግልጽ እናያለን።

እኛስ ምን ያህል የበለጠ ይህንን የታዛዥነት ምሳሌ መከተል ይገባናል? ኢየሱስ ያስተማረንን ይህንን ታላቅ የታዛዥነት ምሳሌ በመከተል፣ ወላጆቻቸውን በሁሉም ነገር የሚታዘዙ ብቻ በእግዚአብሔር ቃልና በዘላለማዊ መርሆዎች ጸንተው በመኖራቸው ታላቅ በረከትና ዋጋ የሚያገኙ መሆኑን ልናስታውስ ይገባል።


ዘፀአት 21:15

“አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ይገደል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 20:12

አባትህንና እናትህን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:30

ስም አጥፊዎች፣ አምላክን የሚጠሉ፣ ተሳዳቢዎች፣ ትዕቢተኞችና ትምክሕተኞች ናቸው፤ ክፋትን የሚሠሩበትን መንገድ ያውጠነጥናሉ፤ ለወላጆቻቸው አይታዘዙም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 5:16

አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 13:1

ጠቢብ ልጅ የአባቱን ምክር በማስተዋል ይሰማል፤ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አያዳምጥም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 1:8

ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:20

ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ትእዛዝ አክብር፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 7:10

ሙሴ፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይሙት’ ብሎ ነበርና፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 13:24

በአርጩሜ ከመቅጣት የሚሳሳለት ልጁን ይጠላል፤ የሚወድደው ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 15:4

እግዚአብሔር፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል’ ብሎ ሲያዝዝ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 19:3

“ ‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤ ሰንበታቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:20

አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፣ መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ ይጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 6:1

ልጆች ሆይ፤ በጌታ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤ ይህ ተገቢ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:20

ልጆች ሆይ፤ ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ በሁሉም ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 27:16

“አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 6:20-21

ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ትእዛዝ አክብር፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው። ምን ጊዜም በልብህ አኑራቸው፤ በዐንገትህም ዙሪያ እሰራቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:1

የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:5

ቂል የአባቱን ምክር ይንቃል፤ መታረምን የሚቀበል ግን አስተዋይነቱን ያሳያል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:20

ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ሰው ግን እናቱን ይንቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 19:26

አባቱን የሚዘርፍ፣ እናቱንም የሚያሳድድ፣ ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 22:6

ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤ በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 23:22

የወለደህን አባትህን አድምጥ፤ እናትህንም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 23:24-25

የጻድቅ ሰው አባት እጅግ ደስ ይለዋል፤ ጠቢብ ልጅ ያለውም በርሱ ሐሤት ያደርጋል። አባት እናትህ ደስ ይበላቸው፤ ወላጅ እናትህም ሐሤት ታድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:7

ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፤ ከሆዳሞች ጋራ ጓደኛ የሚሆን ግን አባቱን ያዋርዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 30:11

“አባቱን የሚረግም፣ እናቱን የማይባርክ ትውልድ አለ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 30:17

“በአባት ላይ የምታፌዝ ዐይን፣ የእናትንም ትእዛዝ የምትንቅ፣ የሸለቆ ቍራዎች ይጐጠጕጧታል፤ ጆፌ አሞሮችም ይበሏታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 12:1

የጭንቀት ጊዜ ሳይመጣ፣ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመታት ሳይደርሱ፣ በወጣትነትህ ጊዜ፣ ፈጣሪህን ዐስብ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:19

ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 22:7

አባቶችና እናቶች በውስጥሽ ተዋረዱ፤ መጻተኞች ተጨቈኑ፤ ድኻ አደጎችና መበለቶች ተንገላቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚልክያስ 1:6

“ልጅ አባቱን፣ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔ አባት ከሆንሁ፣ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ የት አለ?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “ካህናት ሆይ፤ ስሜን የምታቃልሉት እናንተ ናችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚልክያስ 4:6

መጥቼ ምድርን በርግማን እንዳላጠፋ፣ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:19

አባትህንና እናትህን አክብር፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 21:28-31

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ምን ይመስላችኋል? ሁለት ወንዶች ልጆች ያሉት አንድ ሰው ነበረ፤ ወደ መጀመሪያው ልጁ ሄዶ፣ ‘ልጄ ሆይ፤ ዛሬ ወደ ወይኑ ቦታ ሄደህ ሥራ’ አለው። “ልጁም፣ ‘አልሄድም’ አለው፤ ኋላ ግን ተጸጽቶ ሄደ። ማንም ሰው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ቢላችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልጋሉ፤ እርሱም ወዲያውኑ መልሶ ይልካቸዋል’ በሉት።” “ወደ ሁለተኛው ልጁ ሄዶ እንደዚያው አለው፤ ልጁም ‘ዕሺ ጌታዬ እሄዳለሁ’ አለው፤ ነገር ግን ሳይሄድ ቀረ። “ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?” እነርሱም፣ “የመጀመሪያው ልጅ” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሟችኋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 10:19

‘አታመንዝር፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ አታታልል፣ አባትህንና እናትህን አክብር’ የሚለውን ትእዛዝ ታውቃለህ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 2:51

ከዚያም ዐብሯቸው ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 18:20

‘አታመንዝር፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ አባትህንና እናትህን አክብር’ የሚለውን ትእዛዝ ታውቃለህ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 19:26-27

በዚያም ኢየሱስ እናቱንና የሚወድደውም ደቀ መዝሙር አጠገቧ ቆሞ ሲያያቸው እናቱን፣ “አንቺ ሴት ሆይ፤ ልጅሽ ይኸው” አላት፤ ደቀ መዝሙሩንም፣ “እናትህ ይህችው” አለው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይህ ደቀ መዝሙር ወደ ቤቱ ወሰዳት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 6:2-3

“አባትህንና እናትህን አክብር” በሚለው ቀዳሚ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ፣ በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና። ስለዚህ መናገር የሚገባኝን ያለ ፍርሀት እንድናገር ጸልዩልኝ። በምን ሁኔታ እንዳለሁና ምን እንደማደርግ ታውቁ ዘንድ ተወዳጅ ወንድምና በጌታ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ቲኪቆስ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል። የእኛን ሁኔታ እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያበረታ ለዚሁ ስል ወደ እናንተ እልከዋለሁ። ከእግዚአብሔር አብ፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም፣ ፍቅርም ከእምነት ጋራ ለወንድሞች ይሁን። ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን። “መልካም እንዲሆንልህ፣ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም” የሚል ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 5:4

አንዲት መበለት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሯት፣ እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ቤተ ሰብ በመርዳትና ለወላጆቻቸውም ብድራትን በመመለስ ከሁሉ በፊት እምነታቸውን በተግባር ለማሳየት መማር ይገባቸዋል፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 5:8

አንድ ሰው ዘመዶቹን፣ በተለይም የቅርብ ቤተ ሰቡን የማይረዳ ከሆነ ሃይማኖቱን የካደ፣ ከማያምንም ሰው ይልቅ የባሰ ክፉ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 5:16

አማኝ የሆነች ማንኛዋም ሴት በቤተ ሰቧ ውስጥ መበለቶች ቢኖሯት፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ መበለቶችን ብቻ መርዳት እንድትችል እርሷው ትርዳቸው እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሸክም እንዲሆኑ አትተዋቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 3:2

ሰዎች ራሳቸውን የሚወድዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወድዱ፣ ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:9

ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:5

ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 21:17

“አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ይገደል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 20:9

“ ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ማንኛውም ሰው ይገደል፤ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና ደሙ በራሱ ላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 21:18-21

አንድ ሰው፣ የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፣ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፣ አባትና እናቱ ይዘው በሚኖሩበት ከተማ በር ወዳሉት አለቆች ያምጡት፤ ሽማግሌዎችህና ዳኞችህ ወጥተው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ አንሥቶ በአቅራቢያው እስካሉት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ። “ይህ ልጃችን እልከኛና ዐመፀኛ ነው፤ አይታዘዘንም፤ አባካኝና ሰካራም ነው” ብለው ለከተማው አለቆች ይንገሯቸው። ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 4:1

ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤ ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 17:20

ዳዊት በማለዳ በጎቹን ለጠባቂ ትቶ፣ እሴይ እንዳዘዘው ዕቃውን ይዞ ጕዞ ጀመረ። ልክ ሰራዊቱ እየፎከረ ለውጊያ ቦታ ቦታውን ለመያዝ በሚወጣበት ጊዜ ከጦሩ ሰፈር ደረሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ሳሙኤል 17:22

ዳዊት ዕቃውን ከስንቅ ጠባቂው ዘንድ አስቀምጦ ወደ ጦሩ ግንባር ሮጠ፤ ወንድሞቹንም አግኝቶ ደኅንነታቸውን ጠየቀ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ነገሥት 2:19

ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጕዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ሄደች፤ ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ፤ እጅ ከነሣትም በኋላ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ንጉሡም ለእናቱ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 35:18-19

ኤርምያስም ሬካባውያንን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአባታችሁን የኢዮናዳብን ትእዛዝ ስለ ጠበቃችሁ፤ መመሪያውን ስለ ተከተላችሁ፤ ያዘዛችሁንም ሁሉ ስለ ፈጸማችሁ’ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን የሚያገለግለኝ ሰው ለዘላለም አይታጣም።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 16:14

የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 12:14

ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ስመጣ በምንም ነገር ሸክም አልሆንባችሁም፤ እኔ እናንተን እንጂ ከእናንተ ምንም አልፈልግምና፤ ደግሞም ወላጆች ለልጆች ገንዘብ ያከማቻሉ እንጂ ልጆች ለወላጆች አያከማቹም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:8

በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ እርስ በርሳችሁ ተሳሰቡ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:10

“ከእነዚህ ከታናናሾች መካከል አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ እላችኋለሁና፤ በሰማይ ያሉት መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉ፤ [

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:23

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የሚወድደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወድደዋል፤ ወደ እርሱ እንመጣለን፤ ከርሱም ጋራ እንኖራለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 2:40

ሕፃኑም እያደገ፣ እየጠነከረም ሄደ፤ በጥበብ ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በርሱ ላይ ነበረ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 2:46-47

ከሦስት ቀንም በኋላ፣ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲያደምጣቸውና ጥያቄ ሲያቀርብላቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ አገኙት፤ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይደነቁ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 15:20-24

ስለዚህም ተነሥቶ ወደ አባቱ ሄደ። “ነገር ግን፣ እርሱ ገና ሩቅ ሳለ፣ አባቱ አይቶት ራራለት፤ ወደ እርሱም እየሮጠ ሄዶ ዐቅፎ ሳመው። “ልጁም፣ ‘አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤ ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው። “አባቱ ግን ባሮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘ፈጥናችሁ ከሁሉ ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤ የሠባውንም ፍሪዳ አምጡና ዕረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት፤ ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶም ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 19:18

ገና ተስፋ ሳለ፣ ልጅህን ሥርዐት አስይዘው፤ ሲሞት ዝም ብለህ አትየው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 22:15

ቂልነት በሕፃን ልብ ታስሯል፤ የተግሣጽ በትር ግን ከርሱ ያርቅለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:15

የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤ መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:17

ልጅህን ቅጣው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ ነፍስህንም ደስ ያሰኛታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:4-7

እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን። በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት! በበረሓስ ምን ያህል አሳዘኑት! ደግመው ደጋግመው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፤ የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጡት። እነርሱን በዚያ ቀን ከጠላት የታደገበትን፣ ያን ኀይሉን አላስታወሱም፤ በግብጽ ያደረገውን ታምራዊ ምልክት፣ በጣኔዎስም በረሓ ያሳየውን ድንቅ ሥራ አላሰቡም። ወንዞቻቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ ከጅረቶቻቸውም መጠጣት አልቻሉም። የዝንብ ሰራዊት ሰደደባቸው፤ ነደፏቸውም፤ ጓጕንቸርም ላከባቸው፤ ሰዎችንም አጠፉ። አዝመራቸውን ለኵብኵባ፣ ሰብላቸውንም ለአንበጣ ሰጠባቸው። የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣ የበለስ ዛፋቸውንም በውርጭ አጠፋ። ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣ የከብት መንጋቸውን ለመብረቅ እሳት ዳረገ። ጽኑ ቍጣውን በላያቸው ሰደደ፤ መዓቱን፣ የቅናቱን ቍጣና መቅሠፍቱን ላከባቸው፤ አጥፊ የመላእክት ሰራዊትም ሰደደባቸው። ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ፤ በእስራኤልም ሕግን ደነገገ፤ ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፣ አባቶቻችንን አዘዘ። ለቍጣው መንገድ አዘጋጀ፤ ነፍሳቸውንም ከሞት አላተረፈም፤ ነገር ግን ሕይወታቸውን ለመቅሠፍት አሳልፎ ሰጠ። የዐፍላ ጕልበታቸው መጀመሪያ የሆኑትን በካም ድንኳን፣ በኵሮቻቸውንም ሁሉ በግብጽ ምድር ፈጀ። ሕዝቡን ግን እንደ በግ አወጣቸው፤ በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው። ያለ ሥጋት መራቸው፤ እነርሱም አልፈሩም፤ ጠላቶቻቸውን ግን ባሕር ዋጣቸው። ቀኝ እጁም ወዳስገኘችው ወደዚህ ተራራ፣ ወደ ቅድስት ምድር አገባቸው። ሕዝቦችን ከፊታቸው አባረረ፤ ምድራቸውን ርስት አድርጎ በገመድ አከፋፈላቸው፤ የእስራኤልንም ነገዶች በጠላቶቻቸው ቤት አኖረ። እነርሱ ግን አምላክን ተፈታተኑት፤ በልዑልም ላይ ዐመፁ፤ ትእዛዙንም አልጠበቁም። ተመልሰው እንደ አባቶቻቸው ከዳተኛ ሆኑ፤ እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ። በኰረብታ ማምለኪያዎቻቸው አስቈጡት፤ ተቀርጸው በተሠሩ ጣዖቶቻቸው አስቀኑት። እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ። ይህም የሚቀጥለው ትውልድ እንዲያውቅ፣ እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው፣ ገና ለሚወለዱትም እንዲነግሩ ነው። በሰዎች መካከል ያቆማትን ድንኳን፣ የሴሎን ማደሪያ ተዋት። የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ። ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤ በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ። ጕልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፤ ልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም። ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤ መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው። ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ጠጅ ስካር እንደ በረደለት ጀግናም ብድግ አለ። ጠላቶቹን መትቶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤ የዘላለም ውርደትም አከናነባቸው። የዮሴፍን ድንኳን ተዋት፤ የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም። ነገር ግን የይሁዳን ነገድ፣ የወደዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ። መቅደሱን እንደ ታላቅ ከፍታ፣ ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት። እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእርሱንም ሥራ አይረሱም፤ ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 6:6-7

ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢያሱ 24:15

እግዚአብሔርን ማምለክ የማያስፈልግ መስሎ ከታያችሁ ግን፣ የቀድሞ አባቶቻችሁ ከወንዙ ማዶ ካመለኳቸው አማልክት ወይም በምድራቸው የምትኖሩባቸው አሞራውያን ከሚያመልኳቸው አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:1-2

ልጄ ሆይ፤ ትምህርቴን አትርሳ፤ ትእዛዞቼን በልብህ ጠብቅ፤ ይህን ብታደርግ፣ ጐተራህ ሞልቶ ይትረፈረፋል፤ መጥመቂያህም በአዲስ የወይን ጠጅ ቲፍ ብሎ ይሞላል። ልጄ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤ በዘለፋውም አትመረር፤ አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ ሁሉ፣ እግዚአብሔርም የሚወድደውን ይገሥጻልና። ብፁዕ ነው፤ ጥበብን የሚያገኛት፣ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው፤ እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና። ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤ አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም። በቀኝ እጇ ረዥም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች። መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው። ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤ የሚይዟትም ይባረካሉ። እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤ በማስተዋል ሰማያትን በየስፍራቸው አጸና፤ ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤ ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 4:10

ልጄ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ ቃሌንም ልብ በል፤ የሕይወት ዘመንህም ትበዛለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 7:1-3

ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ጠብቅ፤ ትእዛዜንም በውስጥህ አኑር። ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ። ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤ እግሮቿ ዐርፈው ቤት አይቀመጡም፤ አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ፣ በየማእዘኑም ታደባለች። አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ ኀፍረቷንም ጥላ እንዲህ አለችው፤ “በቤቴ የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ፤ ስለዚህ አንተን ለማግኘት ወጣሁ፤ ፈልጌህ ነበር፤ ይኸው አገኘሁህ። ዐልጋዬን ከግብጽ የመጣ፣ ጌጠኛ በፍታ አልብሼዋለሁ። ዐልጋዬን፣ የከርቤ፣ የአደስና የቀረፋ ሽቱ አርከፍክፌበታለሁ። ና፤ እስኪነጋ በጥልቅ ፍቅር እንርካ፤ በፍቅር ራሳችንን እናስደስት። ባሌ እቤት የለም፤ ሩቅ አገር ሄዷል። ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው። በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን አይመለስም።” በሚያግባቡ ቃላት አሳተችው፤ በለሰለሰ አንደበቷ አታለለችው። ለዕርድ እንደሚነዳ በሬ፣ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ አጋዘን፣ ሳያንገራግር ተከተላት፤ ፍላጻ ጕበቱን እስኪወጋው ድረስ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ፣ በርራ ወደ ወጥመድ እንደምትገባ ወፍ ሆነ። ልጆቼ ሆይ፤ አሁንም አድምጡኝ፤ የምለውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ። ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ፤ ወደ ስሕተት ጐዳናዋም አትግቡ። አዋርዳ የጣለቻቸው ብዙ ናቸው፤ የገደለቻቸውም ስፍር ቍጥር የላቸውም። ቤቷ ወደ ሲኦል የሚወስድ፣ ወደ ሞት ማደሪያም የሚያወርድ ጐዳና ነው። በጣትህ ላይ እሰረው፤ በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 8:32-33

“እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ መንገዴን የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው። ምክሬን አድምጡ፤ ጥበበኞች ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:29

ቤተ ሰቡን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፤ ቂልም ሰው የጠቢብ ባሪያ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 127:3-5

እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤ የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው። በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣ በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው። ብፁዕ ነው፤ ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ ሰው፤ ከጠላቶቻቸው ጋራ በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:3-4

ቤት በጥበብ ይሠራል፤ በማስተዋልም ይጸናል፤ በሰነፍ ሰው ዕርሻ በኩል ዐለፍሁ፤ በልበ ቢስ ሰው የወይን ቦታ ዐልፌ ሄድሁ፤ በያለበት እሾኽ በቅሎበታል፤ መሬቱም ዐረም ለብሷል፤ ቅጥሩም ፈራርሷል። ያየሁትን ነገር አወጣሁ፣ አወረድሁ፤ ካስተዋልሁትም ትምህርት አገኘሁ፤ ጥቂት ማንቀላፋት፤ ጥቂት ማንጐላጀት፤ እጅን አጣጥፎ ጥቂት ጋደም ማለት፤ ድኽነት እንደ ወንበዴ፣ ዕጦትም መሣሪያ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። በዕውቀትም ውድና ውብ በሆነ ንብረት፣ ክፍሎቹ ይሞላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:3

ጥበብን የሚወድድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤ የአመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 3:4

ልጆቹን ታዛዥና አክባሪ አድርጎ በማሳደግ የገዛ ቤተ ሰቡን በአግባቡ የሚያስተዳድር ሊሆን ይገባል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 3:12

ዲያቆናት የአንዲት ሚስት ባል መሆን ይገባቸዋል፤ ደግሞም ልጆቻቸውንና ቤተ ሰቦቻቸውን በአግባቡ የሚያስተዳድሩ መሆን አለባቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:7-8

በማንኛውም ነገር መልካም የሆነውን ነገር በማድረግ ራስህን አርኣያ አድርገህ አቅርብላቸው። በምታስተምራቸውም ትምህርት ጭምተኛነትን፣ ቁም ነገረኛነትን፣ የማይነቀፍ ጤናማ አነጋገርንም አሳይ፤ ይኸውም ተቃዋሚ ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር በማጣት እንዲያፍር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:17

ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጕዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው፤ አለዚያ አይበጃችሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:3

እግዚአብሔርን መውደድ ትእዛዞቹን መፈጸም ነውና። ትእዛዞቹም ከባድ አይደሉም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 18:19-24

ምክር እሰጥሃለሁና አሁን እኔን ስሙኝ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይሁን። አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝብን የምትወክል መሆን አለብህ፤ ክርክራቸውን ወደ እርሱ ታቀርባለህ። ሙሴ ሚስቱን ሲፓራን ከመለሳት በኋላ ዐማቱ ዮቶር እርሷንና ሁለት ወንድ ልጆቿን ተቀብሏቸው ነበር። ሥርዐቶቹንና ሕጎቹን አስተምራቸው፤ እንዴት መኖር እንዳለባቸውና ምን መሥራት እንደሚገባቸው አሳያቸው። ነገር ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞችና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ። የሺሕ፣ የመቶ፣ የዐምሳ፣ የዐሥር፣ አለቃ አድርገህ ሹማቸው። በማንኛውም ጊዜ ሕዝቡን ይዳኙ፤ ቀላሉን ነገር እነርሱ ይወስኑ፤ አስቸጋሪ የሆነውን ጕዳይ ሁሉ ግን ለአንተ እንዲያቀርቡ አድርግ፤ ሥራውን ስለሚያግዙህ ሸክምህ ይቃለላል። አንተ ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም ይህንኑ ቢያዝዝህ፣ ድካምህን መቋቋም ትችላለህ፤ እነዚህም ሰዎች ሁሉ ረክተው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።” ሙሴ ዐማቱን ሰማ፤ ያለውንም ሁሉ ፈጸመ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ሳሙኤል 7:14

አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል ቢፈጽም ግን ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 2:1-2

ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ብትቀበል፣ ትእዛዜንም በልብህ ብታኖር፣ ጥበብ ልብህ ውስጥ ትገባለችና፤ ዕውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፤ የመለየት ችሎታ ይጋርድሃል፤ ማስተዋልም ይጠብቅሃል። ጥበብ ንግግራቸው ጠማማ ከሆነ ሰዎች፣ ከክፉዎችም መንገድ ታድንሃለች፤ እነዚህም በጨለማ መንገድ ለመሄድ፣ ቀናውን ጐዳና የሚተዉ ናቸው፤ ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው፣ በክፋት ጐዳና ሐሤት የሚያደርጉ፣ መንገዳቸው ጠማማ፣ በአካሄዳቸው ጠመዝማዞች ናቸው። ከአመንዝራ ሴትም ትጠብቅሃለች፤ በአንደበቷም ከምታታልል ባዕድ ታድንሃለች፤ ይህችም የልጅነት ባሏን የተወች፣ በአምላኳ ፊት የገባችውን ኪዳን ያቃለለች ናት። ቤቷ ወደ ሞት ያደርሳል፤ መንገዷም ወደ መናፍስተ ሙታን ያመራል። ወደ እርሷ የሚገባ ማንም አይመለስም፤ የሕይወትንም መንገድ አያገኝም። ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል ብትመልስ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 19:18-19

ገና ተስፋ ሳለ፣ ልጅህን ሥርዐት አስይዘው፤ ሲሞት ዝም ብለህ አትየው። ግልፍተኛ ሰው ቅጣትን መቀበል ይገባዋል፤ በምሕረት ካለፍኸው ሌላም ጊዜ አይቀርልህም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 1:10

ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣ ዕሺ አትበላቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 18:20

ሥርዐቶቹንና ሕጎቹን አስተምራቸው፤ እንዴት መኖር እንዳለባቸውና ምን መሥራት እንደሚገባቸው አሳያቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 10:5

በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:1

ማንኛውም ሰው በሥልጣን ላሉት ሹማምት መገዛት ይገባዋል፤ ከእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣናት በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:11

ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 8:29

የላከኝ እርሱ ከእኔ ጋራ ነው፤ ምን ጊዜም የሚያስደስተውን ስለማደርግ ብቻዬን አልተወኝም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 1:5-6

በዚህም ምክንያት በሙሉ ትጋት በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ለመጨመር ጣሩ፤ በበጎነት ላይ ዕውቀትን፣ በዕውቀት ላይ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛት ላይ መጽናትን፣ በመጽናት ላይ እውነተኛ መንፈሳዊነትን፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:17

ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:11-12

ልጄ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤ በዘለፋውም አትመረር፤ አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ ሁሉ፣ እግዚአብሔርም የሚወድደውን ይገሥጻልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 2:52

ኢየሱስም በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት አደገ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:9

ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:12-13

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በእናንተ መካከል በትጋት የሚሠሩትን፣ በጌታም የበላዮቻችሁና መካሪዎቻችሁ የሆኑትን እንድታከብሯቸው እንለምናችኋለን፤ ስለ ሥራቸውም በፍቅር እጅግ አክብሯቸው። እርስ በርሳችሁም በሰላም ኑሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 103:13

አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር አባታችን ሆይ፤ አንተ ለወላጆች ታላቅ የታዛዥነት ምሳሌ ነህ። ፈቃድህም እንደ አንተ እንድንሆን፥ ታዛዥና ተገሣጭ ልብ ያላቸው፥ ሥርዓትህንና ሕግጋትህን የምናከብር፥ የወላጆችንም እያንዳንዱን ትምህርትና ምክር የምንጠብቅ ልጆች እንድንሆን እንደሆነ እናውቃለን። ልጆች ቃልህን የሚያስተውልና የሚታዘዝ ልብ እንዲኖራቸው እንለምንሃለን። የመንፈስ ቅዱስህ ህልውና በየዕለቱ ወላጆቻቸውን ለማክበርና በአግባቡ ለመያዝ የሚያስችል ጥበብ ይስጣቸው። የልጆች ልብ በአክብሮት፥ በታዛዥነትና በትህትና ወደ ወላጆቻቸው ይመለስ፤ ረጅምና ድል አድራጊ ሕይወት እንዲኖሩም እንጸልያለን። በቃልህም "እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላክህም በሚሰጥህ ምድር ላይ መልካም እንዲሆንልህ" ብለሃል። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ የልጆችን ሕይወት ነጻ አውጣና አድስ፤ የማመፅን፥ የትዕቢትን፥ የግትርነትንና የአለመታዘዝን ሀሳብ ሁሉ ከእነርሱ አርቅ። ፊትህን የመፈለግና በቃልህ የማሰላሰል ጉጉትን በውስጣቸው አኑር፤ ሕይወታቸው ተለውጦ በአንተ እንዲመራ አድርግ። በኢየሱስ ስም፤ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች