Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


106 ጥቅሶች፡ ቂም በመያት ላይ

106 ጥቅሶች፡ ቂም በመያት ላይ

በሕይወታችን ውስጥ የሚያሳዝኑን እና የሚያስከፉን ነገሮች ይደርሱብናል፤ ይህም ቂም በልባችን እንዲያድር ሊያደርገን ይችላል። ምንም እንኳን ይህ አይጠቅመንም ብናውቅም፤ አንዳንድ ጊዜ ያለፈውን እያሰብን ቂም ይዘን እንቀጥላለን፤ ይህ ደግሞ ራሳችንን እንደምንጎዳ አንረዳም።

ቂም በነፍሳችን ላይ ቁስል እንደሚፈጥር እናውቃለን፤ ነገር ግን በአጠቃላይ በአካላችንና በመላ ሰውነታችን ላይም ተጽዕኖ ያሳድራል። እግዚአብሔር ይቅርታን እንድናደርግ ይፈልጋል፤ ምክንያቱም ይህ ለልባችን ጥሩ እንደሆነ ያውቃል። ይቅርታ ማለት ራስን ዝቅ ማድረግ ሳይሆን፤ በነፃነት እንድንኖር የሚያስችለን የጀግንነት ተግባር ነው።

የተጎዳን ከሆነ ይቅር ማለት እና ይቅርታ መጠየቅ አለብን፤ ምሬት እንዲቆጣጠረን ወይም ቂም በውስጣችን እንዲያቆጠቁጥ መፍቀድ የለብንም። እግዚአብሔር ይቅር እንዳለን ሁሉ እኛም እርስ በርሳችን ይቅር ማለት አለብን፤ የእርሱንም ታላቅ ፍቅር እንዲሁ እናጣጥማለን።

ኩራታችን ሲነኩብን ወይም ሲበድሉን መበሳጨታችን የተለመደ ነው። ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀል ላይ የተናገረውን እናስታውስ፦ «አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው» (ሉቃስ 23:34)። ኢየሱስ ይቅር ካለ፤ እኛም ይቅር ማለት እንችላለን።


1 ተሰሎንቄ 5:15

ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁልጊዜ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 19:18

“ ‘ወገንህን አትበቀል፤ ወይም በመካከልህ ከሚኖር በማንኛውም ሰው ላይ ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:22

“ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤ እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:13

እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:15

ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት፣ ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:12

እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 6:37

“አትፍረዱ፤ አይፈረድባችሁም፤ አትኰንኑ፤ አትኰነኑም። ይቅር በሉ፤ ይቅር ትባላላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 23:34

ኢየሱስም፣ “አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ። እነርሱም ልብሱን በዕጣ ተከፋፈሉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 11:25

እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፣ የሰማዩ አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፣ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ። [

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 5:2

ቂሉን ሰው ብስጭት ይገድለዋል፤ ቂሉንም ቅናት ያጠፋዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:31-32

መራርነትን ሁሉ፣ ቍጣና ንዴትን፣ ጭቅጭቅና ስድብን ከማንኛውም ክፋት ጋራ ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ። እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ፣ እናንተም ይቅር ተባባሉ፤ እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:24

የጌታም ባሪያ ሊጣላ አይገባውም፤ ይልቁን ለሰው ሁሉ ገር፣ ለማስተማር ብቃት ያለው፣ ትዕግሥተኛም መሆን ይገባዋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:14-15

እናንተ የበደሏችሁን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ ደግሞ እናንተን ይቅር ይላችኋል። ነገር ግን የሰዎችን በደል ይቅር የማትሉ ከሆነ፣ አባታችሁም በደላችሁን ይቅር አይልላችሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:23

ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራ ሲደርስበት አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:8

ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤ ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 13:4-5

ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 27:41

አባቱ ያዕቆብን ስለ መረቀው፣ ዔሳው በያዕቆብ ላይ ቂም ያዘ፤ በልቡም፣ “ግድ የለም፤ የአባቴ መሞቻው ተቃርቧል፤ ከልቅሶው በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድላለሁ” ብሎ ዐሰበ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:12

ጥላቻ ጠብን ያነሣሣል፤ ፍቅር ግን ስሕተትን ሁሉ ይሸፍናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 50:15

የዮሴፍ ወንድሞች ከአባታቸው ሞት በኋላ፣ “ከፈጸምንበት በደል የተነሣ ዮሴፍ ቂም ይዞ ቢበቀለን ምን እናደርጋለን?” ተባባሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:17

ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤ ጨካኝ ግን በራሱ ላይ መከራ ያመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:10

እያንዳንዱ ልብ የራሱን መራራ ሐዘን ያውቃል፤ ደስታውንም ማንም ሊጋራው አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:29

ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ያሳያል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:1

የለዘበ መልስ ቍጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቍጣን ይጭራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:18

ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:32

ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጕልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 17:9

በደልን የሚሸፍን ፍቅርን ያዳብራል፤ ነገርን የሚደጋግም ግን የልብ ወዳጆችን ይለያያል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 17:14

ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 19:11

ጥበብ ሰውን ታጋሽ ታደርገዋለች፤ በደልን ንቆ መተውም መከበሪያው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:17

ጠላትህ ሲወድቅ ደስ አይበልህ፤ ሲሰናከልም ልብህ ሐሤት አያድርግ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:29

“በእኔ ላይ እንደ ሠራብኝ እሠራለታለሁ፤ ስለ አድራጎቱም የእጁን እመልስለታለሁ” አትበል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 25:21-22

ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም ውሃ አጠጣው። ይህን በማድረግህም፣ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህ፤ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይከፍልሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 7:9

የሞኞች ቍጣ በዕቅፋቸው ውስጥ ስለ ሆነ፣ በመንፈስህ ለቍጣ አትቸኵል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 10:4

የገዥ ቍጣ በተነሣብህ ጊዜ፣ ስፍራህን አትልቀቅ፤ ትዕግሥት ታላቁን ጥፋት ጸጥ ያደርጋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 43:25

“ስለ ራሴ ስል መተላለፍህን የምደመስስልህ፣ እኔ፣ እኔው ነኝ፤ ኀጢአትህን አላስባትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 55:7

ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሐሳቡን ይተው። ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 31:34

ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚክያስ 7:18-19

የርስቱን ትሩፍ ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? ለዘላለም አትቈጣም፤ ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል። ተመልሰህ ትራራልናለህ፤ ኀጢአታችንን በእግርህ ትረግጣለህ፤ በደላችንንም ሁሉ ወደ ጥልቁ ባሕር ትጥላለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:7

ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:9

ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:21-22

“ለቀደሙት ሰዎች፣ ‘አትግደል፤ የገደለ ይፈረድበታል’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወንድሙን ያለ አግባብ የሚቈጣ ይፈረድበታል፤ ማንም ወንድሙን ‘ጅል’ የሚል በሸንጎ ፊት ይጠየቅበታል፤ ‘ደደብ’ የሚለው ደግሞ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይጠብቀዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:23-24

“ስለዚህ መባህን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር በምታቀርብበት ጊዜ፣ ወንድምህ የተቀየመብህ ነገር መኖሩ ትዝ ቢልህ፣ መባህን በዚያው በመሠዊያው ፊት ተወው፤ በመጀመሪያ ሄደህ ከወንድምህ ጋራ ተስማማ፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን ለእግዚአብሔር አቅርብ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:38-39

“ ‘ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ‘ክፉ አድራጊውን ሰው አትቃወሙት’፤ ነገር ግን ቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ጕንጭህን ደግሞ አዙርለት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:43-44

“ ‘ባልንጀራህን ውደድ፤ ጠላትህን ጥላ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ እላችኋለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:1-2

“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ ወይም ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጥ ይኖራልን? እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ የሰማዩ አባታችሁ ታዲያ ለሚለምኑት መልካም ስጦታን እንዴት አብልጦ አይሰጥ? ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና። “በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። “በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው መካከላችሁ በመግባት ከሚያሸምቁ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ። በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾኽ ቍጥቋጦ ወይን፣ ከኵርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁም ጥሩ ዛፍ ሁሉ ጥሩ ፍሬ፣ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል። ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ፣ መጥፎም ዛፍ ጥሩ ፍሬ ማፍራት አይችልም። ጥሩ ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። በምትፈርዱበትም ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:21-22

በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “ጌታ ሆይ፤ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?” አለው። ኢየሱስም “እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:33-35

እኔ እንደ ማርሁህ አንተም ባልንጀራህን ልትምረው አይገባህም ነበርን?’ በቍጣም ያለበትን ዕዳ ከፍሎ እስኪጨርስ ድረስ ለአሳሪዎች አሳልፎ ሰጠው። “ስለዚህ እያንዳንዳችሁ ወንድሞቻችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ፣ የሰማዩ አባቴም እንደዚሁ ያደርግባችኋል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 6:27-28

“ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ፤ የሚረግሟችሁን መርቁ፤ ለሚበድሏችሁም ጸልዩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 6:35-36

ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ መልሳችሁ ለመቀበል ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፤ በዚህም ወሮታችሁ ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና። አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ እናንተም ርኅሩኆች ሁኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 11:4

በደላችንን ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና። ወደ ፈተናም አታግባን፤ ከክፉው አድነን እንጂ።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 17:3-4

ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። “ወንድምህ ቢበድል ገሥጸው፤ ቢጸጸት ይቅር በለው። “የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንደዚሁ ይሆናል። በዚያ ቀን በቤቱ ጣራ ላይ ያለ፣ ማንም ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ለመውሰድ አይውረድ፤ እንዲሁም በዕርሻ ቦታ ያለ ሰው ወደ ኋላው አይመለስ። የሎጥን ሚስት አስታውሱ። ነፍሱን ለማሰንበት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ነፍሱን የሚያጠፋት ግን ያቈያታል። እላችኋለሁ፤ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ይተኛሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። ሁለት ሴቶች ዐብረው ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ ትቀራለች [ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ቦታ ዐብረው ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።”] እነርሱም መልሰው፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወሰዱት ወዴት ነው?” አሉት። እርሱም፣ “በድን ባለበት አሞሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው። በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ፣ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር በለው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 13:34-35

“አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 15:12

ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:8

ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:14

የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:17-19

ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ። ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ። ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:20-21

ይልቁንስ፣ “ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም አጠጣው። ይህን በማድረግህም የእሳት ፍም በራሱ ላይ ትከምራለህ።” ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 14:10

ታዲያ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? ለምንስ ወንድምህን ትንቃለህ? ሁላችንም በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እንቀርባለንና፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 14:13

ስለዚህ እርስ በርሳችን፣ አንዱ በሌላው ላይ ከመፍረድ እንቈጠብ፤ በዚህ ፈንታ ግን በወንድምህ መንገድ ላይ የማሰናከያ ድንጋይ ወይም ወጥመድ እንዳታስቀምጥ ቍርጥ ሐሳብ አድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 16:14

የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 2:5-8

ማንም ሰውን ቢያሳዝን፣ ነገር ማግነን አይሁንብኝና፣ ያሳዘነው እኔን ብቻ ሳይሆን በመጠኑም ቢሆን ሁላችሁንም ነው። እንደዚህ ያለው ሰው ብዙዎች የወሰኑበት ቅጣት በቂው ነው። ደግሞም ከልክ በላይ ዐዝኖ ተስፋ እንዳይቈርጥ፣ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባችኋል። ስለዚህ አሁንም የምትወድዱት መሆናችሁን እንድትገልጹለት እለምናችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 2:10-11

እናንተ ይቅር የምትሉትን ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ፤ በርግጥ ይቅር የምለው ነገር ካለ፣ በክርስቶስ ፊት ይቅር የምለው ስለ እናንተ ስል ነው። ይህንም የምናደርገው ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤ የርሱን ዕቅድ አንስተውምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:14-15

ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ተጠቃሏል፤ ይኸውም፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚል ነው። ነገር ግን እርስ በርሳችሁ የምትነካከሱና የምትበላሉ ከሆነ፣ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19-21

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:22-23

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው። እንደነዚህ ያሉትንም የሚከለክል ሕግ የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:2-3

ፍጹም ትሑታንና ገሮች ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁም በፍቅር እየተቻቻላችሁ ትዕግሥተኞች ሁኑ። እናንተ ግን ክርስቶስን ያወቃችሁት እንደዚህ ባለ መንገድ አይደለም፤ በርግጥ ስለ እርሱ ሰምታችኋል፤ በኢየሱስም እንዳለው እውነት በርሱ ተምራችኋል። ቀድሞ ስለ ነበራችሁበት ሕይወትም፣ በሚያታልል ምኞቱ የጐደፈውን አሮጌ ሰውነታችሁን አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤ ደግሞም በአእምሯችሁ መንፈስ እንድትታደሱ፣ እውነተኛ በሆነው ጽድቅ እንዲሁም ቅድስና እግዚአብሔርን እንዲመስል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው። ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋራ እውነትን ተነጋገሩ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ነንና። “ተቈጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ፤” በቍጣችሁ ላይ ፀሓይ አይግባ፤ ለዲያብሎስም ስፍራ አትስጡት። ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም። እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ። በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:26-27

“ተቈጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ፤” በቍጣችሁ ላይ ፀሓይ አይግባ፤ ለዲያብሎስም ስፍራ አትስጡት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:29-32

እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ። በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ። መራርነትን ሁሉ፣ ቍጣና ንዴትን፣ ጭቅጭቅና ስድብን ከማንኛውም ክፋት ጋራ ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ። እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ፣ እናንተም ይቅር ተባባሉ፤ እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:3-4

ሌሎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትሕትና ቍጠሩ እንጂ፣ በራስ ወዳድነት ምኞት ወይም ከንቱ ውዳሴ ለማግኘት አንዳች አታድርጉ። እርሱም እናንተ ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት ለማሟላት ሲል ለሕይወቱ እንኳ ሳይሣሣ፣ ለክርስቶስ ሥራ ከሞት አፋፍ ደርሶ ነበርና። እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳችሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:14-15

ማንኛውንም ነገር ሳታጕረመርሙና ሳትከራከሩ አድርጉ፤ ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:8

አሁን ግን ቍጣን፣ ንዴትን፣ ክፋትን፣ ስድብንና አሳፋሪ ንግግርን የመሳሰሉትንም ሁሉ አስወግዱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:12-14

እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤ እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ። በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 1:5

የዚህ ትእዛዝ ዐላማ ግን ከንጹሕ ልብ፣ ከበጎ ኅሊና እንዲሁም ከእውነተኛ እምነት የሚገኝ ፍቅር ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:24-26

የጌታም ባሪያ ሊጣላ አይገባውም፤ ይልቁን ለሰው ሁሉ ገር፣ ለማስተማር ብቃት ያለው፣ ትዕግሥተኛም መሆን ይገባዋል፤ እውነትን ወደ ማወቅ ይደርሱ ዘንድ፣ እግዚአብሔር ንስሓን እንደሚሰጣቸው ተስፋ በማድረግ የሚቃወሙትን በየዋህነት የሚያቃና መሆን ይኖርበታል፤ ይኸውም ወደ አእምሯቸው ይመለሳሉ፤ ፈቃዱን ሊያስፈጽማቸው ምርኮኛ አድርጎ ከያዛቸው ከዲያብሎስ ወጥመድም ያመልጣሉ በማለት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:30

“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:14-15

ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ለመኖር የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ለመቀደስም ፈልጉ፤ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት አይችልም። ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት፣ ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:18-19

ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፣ ወደ ጨለማው፣ ወደ ጭጋጉና ወደ ዐውሎ ነፋሱ አልደረሳችሁም፤ ወደ መለከት ድምፅ ወይም ቃልን ወደሚያሰማ ድምፅ አልመጣችሁም፤ የሰሙትም ሌላ ቃል ተጨምሮ እንዳይናገራቸው ለመኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:25

የሚናገረውን እርሱን እንቢ እንዳትሉት ተጠንቀቁ። እነዚያ ከምድር ሆኖ ሲያስጠነቅቃቸው የነበረውን እንቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፣ እኛ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ከርሱ ብንርቅ እንዴት ልናመልጥ እንችላለን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:19-20

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህን አስተውሉ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየ፣ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ ወንድሞቼ ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 3:14-16

ነገር ግን መራራ ቅናትና ራስ ወዳድነት በልባችሁ ቢኖር ኵራት አይሰማችሁ፤ እውነትንም አትካዱ። እንዲህ ያለችዋ ጥበብ ከላይ አይደለችም፤ ነገር ግን ከምድር፣ ከሥጋና ከአጋንንት ናት። ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይገኛሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:1-3

በእናንተ መካከል ያለው ጦርነትና ጠብ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ከሚዋጉት ከምኞቶቻችሁ አይደለምን? በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፣ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል። ወንድሞች ሆይ፤ እርስ በርሳችሁ አትወነጃጀሉ፤ ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙም ላይ የሚፈርድ በሕግ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል። በሕግ ላይ ብትፈርድ ፈራጅ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ሊያድንና ሊያጠፋ የሚችል ነው፤ ነገር ግን በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? እናንተ፣ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ወይም ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በርሷም አንድ ዓመት እንቈያለን፤ እንነግዳለን፤ እናተርፋለንም” የምትሉ እንግዲህ ስሙ። ነገ የሚሆነውን እንኳ አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድን ናት? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁ። ይልቁንም፣ “የጌታ ፈቃድ ቢሆን እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል። አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲህ ያለው ትምክሕት ሁሉ ክፉ ነው። እንግዲህ መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ እንዳለበት እያወቀ የማያደርግ ሰው ኀጢአት ያደርጋል። ትመኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙም። ትገድላላችሁ፤ በብርቱም ትመኛላችሁ፤ ልታገኙም አትችሉም። ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ፤ አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም። ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፣ ለራሳችሁ ሥጋዊ ደስታ በማሰብ በክፉ ምኞት ትለምናላችሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 5:9

ወንድሞች ሆይ፤ እርስ በርሳችሁ አታጕረምርሙ፤ አለዚያ ይፈረድባችኋል፤ እነሆ፤ ፈራጁ በበር ላይ ቆሟል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:8-9

በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ እርስ በርሳችሁ ተሳሰቡ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ። ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች እያደረጋችሁ በረከትን ለመውረስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 4:8

ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና፣ ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:5-6

ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።” ስለዚህ እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:9

በብርሃን አለሁ የሚል፣ ወንድሙን ግን የሚጠላ አሁንም በጨለማ ውስጥ አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:11

ነገር ግን ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው፤ በጨለማ ይመላለሳል፤ ጨለማው ስላሳወረውም የት እንደሚሄድ አያውቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:15

ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳይም የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:7-8

ወዳጆች ሆይ፤ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል። የማይወድድ ግን እግዚአብሔርን አያውቅም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:20-21

ማንም፣ “እግዚአብሔርን እወድደዋለሁ” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፣ እርሱ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና። እርሱም “እግዚአብሔርን የሚወድድ ሁሉ ወንድሙን መውደድ ይገባዋል” የሚለውን ይህን ትእዛዝ ሰጥቶናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:18-19

ይህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በክርስቶስ አማካይነት ከራሱ ጋራ አስታረቀን፤ የማስታረቅንም አገልግሎት ሰጠን፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋራ ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 13:11

በተረፈ ወንድሞች ሆይ፤ ደኅና ሁኑ፤ ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ አንድ ሐሳብ ይኑራችሁ፤ በሰላምም ኑሩ። የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋራ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 1:7

በርሱም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአት ይቅርታ አገኘን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:10

የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከርሱ ጋራ ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 86:5

ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 15:20-24

ስለዚህም ተነሥቶ ወደ አባቱ ሄደ። “ነገር ግን፣ እርሱ ገና ሩቅ ሳለ፣ አባቱ አይቶት ራራለት፤ ወደ እርሱም እየሮጠ ሄዶ ዐቅፎ ሳመው። “ልጁም፣ ‘አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤ ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው። “አባቱ ግን ባሮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘ፈጥናችሁ ከሁሉ ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤ የሠባውንም ፍሪዳ አምጡና ዕረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት፤ ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶም ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 133:1

ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:7

የሰው መንገድ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሠኘው፣ ጠላቶቹ እንኳ ዐብረውት በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:18

ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:11

ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:15

“ወንድምህ ቢበድልህ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻ ሆናችሁ ጥፋቱን ንገረው። ቢሰማህ፣ ወንድምህን እንደ ገና የራስህ ታደርገዋለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 15:7

እንግዲህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሆን ዘንድ ክርስቶስ እንደ ተቀበላችሁ፣ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 1:9

ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 13:10

ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ መፈጸሚያ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:18

“ኑና እንዋቀሥ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ፣ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም፣ እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 3:16

በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

አባቴ ሆይ፥ ሁሉንም ታውቃለህ፤ የልቤንም ጥልቅ ታውቃለህ። በአሰቃቂ ገጠመኞችና በመጥፎ ልምዶች ምክንያት ስህተት እንደሠራሁ አውቃለሁ፤ በዚህም ምክንያት ቂምና ጥላቻ ወደ ልቤ ገብቶ እንዲበክል ፈቅጃለሁ። ቃልህ እንዲህ ይላልና፥ "እንዳይሆን ማንም የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዳያጣ፥ የምሬት ሥር በቅሎ እንዳያናውጻችሁ፥ በእርስዋም ብዙዎች እንዳይበከሉ ተጠንቀቁ።" ጌታ ሆይ፥ ዛሬ በደል ያደረሰብኝን ይቅር ለማለትና በሕመም የተጎዳውን ልቤን ለመፈወስ ወደ አንተ ለመቅረብ ወስኛለሁ። የመንፈስ ቅዱስህ እርዳታ ከሌለኝ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ራሴን ማላቀቅ እንደማልችል ተረድቻለሁ። ሕይወቴን የመለወጥና የመቀየር ኃይል ያለህ አንተ ብቻ ነህና። ክፉ ላደረሰብኝ ሰው ፍቅር እንዳፈስና እንድጸልይለት ልቤን ክፈትልኝ፤ በዚህም ምክንያት ከአንተ ጋር ያለኝን ግንኙነት መልሼ እንዳገኝ እርዳኝ። በኢየሱስ ስም። አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች