Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


105 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ለአምላክ ያልሆኑ

105 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ለአምላክ ያልሆኑ

እግዚአብሔርን አውቄ፣ ፍቅሩንም ቀምሼ ሰማያዊውን የዘላለም ሕይወት ተስፋ ይዤ፣ አንዳንዶች እግዚአብሔርን አለመቀበል ለምን እንደሚመርጡ ለመረዳት አዳጋች ሆኖብኛል።

ግን ኃጢአት በአዕምሮና በልብ ላይ ስላለው ተጽዕኖ ስናስብ፣ እግዚአብሔርን የማያምኑ ሰዎች ለምን እንደዚህ አይነት አቋም እንደሚይዙ መገንዘብ እንችላለን። ስለእነሱ መጸለይ ይጠበቅብናል። እግዚአብሔርን እንዳያዩ የሚያግዳቸው መጋረጃ ተነስቶ፣ በሕይወታቸው ውስጥ በግልጽ እንዲገለጥላቸው፣ የልቦና ዓይናቸውንም እንዲከፍትላቸው መጸለይ አለብን።

ወደ እነዚህ ሰዎች ስንቀርብ፣ በቃላት ብቻ መተማመን የለብንም። የወንጌልን የለውጥ ኃይል በሕይወታችን ማሳየት አለብን። በዚህ መንገድ፣ የክርስቶስን እውነተኛነት ያምናሉ። ክርክር ውስጥ መግባት ወይም መከራከር አይጠበቅብንም። ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስን ግልጽ ማስረጃ በማሳየት፣ ፍጹሙን እውነት ለእነርሱ ማካፈል ይገባናል።


ሮሜ 1:20

ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የማይታየው የእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ይኸውም ዘላለማዊ ኀይሉና መለኮትነቱ፣ ከፍጥረቱ በግልጽ ይታያል፤ ስለዚህ ሰዎች ማመካኛ የላቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:8

በክርስቶስ ላይ ሳይሆን፣ በሰዎች ወግና በዚህ ዓለም መሠረታዊ መንፈሳዊ ኀይሎች ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማግባቢያ ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:22

“ባል በሞተባት ወይም አባትና እናት በሌለው ልጅ ላይ ግፍ አትዋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 6:44

የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ማንም ወደ እኔ መምጣት አይችልም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:19

ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው ለእነርሱ ግልጽ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለእነርሱ ግልጽ አድርጎታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 2:14

መንፈሳዊ ያልሆነ ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የሆነውን ነገር ሊቀበል አይችልም፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ነገር ለርሱ ሞኝነት ነው፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ፣ ሊረዳው አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 10:18

እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤ መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወድዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 68:5

እግዚአብሔር በተቀደሰ ማደሪያው፣ ለድኻ አደጉ አባት፣ ለባልቴቲቱም ተሟጋች ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 2:14

ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ሕግ የሚያዝዘውን ነገር በተፈጥሮ ሲያደርጉ፣ ሕግ ባይኖራቸውም እነርሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 14:1

ሞኝ በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ጸያፍ ነገሮችን ይሠራሉ። በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 146:9

እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ ድኻ አደጎችንና መበለቶችን ይደግፋል፤ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:25

እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ቤት ያፈርሰዋል፤ የመበለቲቱን ዳር ድንበር ግን እንዳይደፈር ይጠብቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 23:10-11

የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ፤ አባት የሌላቸውንም ልጆች መሬት አትግፋ፤ ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፤ እርሱ ይፋረድላቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:21

እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:17

መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፣ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 10:2

የድኾችን መብት ለሚገፍፉ፣ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 53:1

ሞኝ በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤ በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 3:34-36

የምድሪቱ እስረኞች ሁሉ፣ በእግር ሲረገጡ፣ በልዑል ፊት፣ ሰው መብቱ ሲነፈገው፣ ሰው ፍትሕ ሲጓደልበት፣ ጌታ እንዲህ ዐይነቱን ነገር አያይምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:18

እነርሱ ከልባቸው መደንደን የተነሣ ስለማያስተውሉ ልቡናቸው ጨልሟል፤ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ተለይተዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 12:7-9

“እስኪ እንስሳትን ጠይቁ፤ ያስተምሯችኋል፤ የሰማይ ወፎችንም ጠይቁ፣ ይነግሯችኋል፤ ለምድር ተናገሩ፤ ታስተምራችኋለች፤ የባሕርም ዓሣ ይነግራችኋል። የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ ከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማን ነው?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 2:36-37

ደግሞም ከአሴር ወገን የሆነች የፋኑኤል ልጅ፣ ሐና የምትባል ነቢይት በዚያ ነበረች፤ እርሷም በጣም አርጅታ ነበር፤ በድንግልናዋ ካገባችው ባሏም ጋራ ሰባት ዓመት የኖረች ነበረች፤ ዕድሜዋም ሰማንያ አራት ዓመት እስኪሆናት ድረስ ቀንና ሌሊት ከቤተ መቅደስ ሳትለይ፣ በጾምና በጸሎት የምታገለግል መበለት ሆና ቈየች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 4:25-26

ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፤ ሰማይ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ተዘግቶ ጽኑ ራብ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በነበረበት በኤልያስ ዘመን፣ ብዙ መበለቶች በእስራኤል ነበሩ፤ ኤልያስ ከእነዚህ መካከል ወደ አንዷም አልተላከም፤ ነገር ግን በሲዶና አገር በሰራፕታ ወደ ነበረችው መበለት ተላከ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 18:1-8

ደቀ መዛሙርቱ ሳይታክቱ ሁልጊዜ መጸለይ እንደሚገባቸው ለማሳየት ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ “ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፣ አንዱ ፈሪሳዊ፣ ሌላው ቀረጥ ሰብሳቢ ነበሩ። ፈሪሳዊውም ቆሞ ስለ ራሱ እንዲህ ይጸልይ ነበር፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ቀማኛ፣ ዐመፀኛ፣ አመንዝራ፣ ይልቁንም እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ባለመሆኔ አመሰግንሃለሁ፤ በሳምንት ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፤ ከማገኘውም ሁሉ ዐሥራት አወጣለሁ።’ “ቀረጥ ሰብሳቢው ግን በርቀት ቆሞ፣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ማየት እንኳ አልፈለገም፤ ነገር ግን ደረቱን እየደቃ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ኀጢአተኛውን ማረኝ’ ይል ነበር። “እላችኋለሁ፤ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይህኛው በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ ተብሎ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይላልና፤ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ግን ከፍ ይላል።” ኢየሱስ እንዲዳስሳቸው ሰዎች ሕፃናትን ወደ እርሱ ያመጡ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ይህን ባዩ ጊዜ ገሠጿቸው። ኢየሱስ ግን ሕፃናቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አለ፤ “ሕፃናት ወደ እኔ እንዲመጡ ፍቀዱላቸው፤ አትከልክሏቸውም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና። እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበል ሁሉ ከቶ አይገባባትም።” ከአይሁድ አለቆች አንዱ፣ “ቸር መምህር ሆይ፤ የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ላድርግ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም፤ እንዲህም አላቸው፤ “በአንዲት ከተማ የሚኖር እግዚአብሔርን የማይፈራና ሰውን የማያከብር አንድ ዳኛ ነበረ። ‘አታመንዝር፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ አባትህንና እናትህን አክብር’ የሚለውን ትእዛዝ ታውቃለህ።” ሰውየውም፣ “እነዚህንማ ከልጅነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ” አለው። ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ “እንግዲያውስ አንድ ነገር ይቀርሃል፤ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድኾች ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ይኖርሃል፤ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው። ሰውየው ግን ይህን ሲሰማ፣ ብዙ ሀብት ስለ ነበረው በጣም ዐዘነ። ኢየሱስም ሰውየውን ተመልክቶ እንዲህ አለ፤ “ለሀብታሞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ምንኛ ከባድ ነው! ሀብታም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።” ይህን የሰሙ ሰዎችም፣ “ታዲያ፣ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ። ኢየሱስም፣ “በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል” አለ። ጴጥሮስም፣ “እነሆ፤ እኛ ያለንን ሁሉ ትተን ተከትለንሃል” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ለእግዚአብሔር መንግሥት ብሎ ቤቱን ወይም ሚስቱን ወይም ወንድሞቹን ወይም ወላጆቹን ወይም ልጆቹን የተወ፣ በዚያችው ከተማ የምትኖር አንዲት መበለት ነበረች፤ እርሷም፣ ‘ከባላጋራዬ ጋራ ስላለብኝ ጕዳይ ፍረድልኝ’ እያለች ወደ እርሱ ትመላለስ ነበር። በዚህ ዘመን ብዙ ዕጥፍ፣ በሚመጣውም ዘመን የዘላለምን ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።” ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻ ወስዶ እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ ነቢያት ስለ ሰው ልጅ የጻፉትም ሁሉ ይፈጸማል። ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነርሱም ያፌዙበታል፤ ያንገላቱታል፤ ይተፉበታል፤ ይገርፉታል፤ ከዚያም ይገድሉታል። እርሱ ግን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ይነሣል።” ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ የተረዱት አንድም ነገር አልነበረም፤ አባባሉም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለ ምን እንደ ተናገረም አላወቁም። ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ፣ አንድ ዐይነ ስውር መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር። ዐይነ ስውሩም ሕዝቡ በዚያ ሲያልፍ ሰምቶ ስለ ሁኔታው ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ እያለፈ ነው” ብለው ነገሩት። እርሱም፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ጮኸ። ከፊት የሚሄዱ ሰዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ። “ዳኛውም ለተወሰነ ጊዜ አልተቀበላትም ነበር፤ በኋላ ግን በልቡ እንዲህ አለ፤ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላከብር፣ ኢየሱስም ቆም ብሎ ሰውየውን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ፤ ወደ እርሱም በቀረበ ጊዜ፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” ብሎ ጠየቀው። ዐይነ ስውሩም፣ “ጌታ ሆይ፤ ዳግም እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው። ኢየሱስም፣ “እይ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው። ሰውየውም ወዲያውኑ ማየት ቻለ፤ እግዚአብሔርንም እያከበረ ኢየሱስን ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። ይህች መበለት ስለምትጨቀጭቀኝ እፈርድላታለሁ፤ አለዚያ ዘወትር እየተመላለሰች ታሰለቸኛለች።’ ” ጌታም እንዲህ አለ፤ “ዐመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔርስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? ከመጠን በላይስ ችላ ይላቸዋልን? እላችኋለሁ፤ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ እምነትን ያገኝ ይሆንን?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 5:3-5

በርግጥ ችግረኛ የሆኑትን መበለቶች ተንከባከባቸው። አንዲት መበለት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሯት፣ እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ቤተ ሰብ በመርዳትና ለወላጆቻቸውም ብድራትን በመመለስ ከሁሉ በፊት እምነታቸውን በተግባር ለማሳየት መማር ይገባቸዋል፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነውና። በርግጥ መበለት የሆነች፣ ብቻዋንም የምትኖር ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ ታደርጋለች፤ ለጸሎትና የእግዚአብሔርን ርዳታ ለመለመን ሌሊትና ቀን ትተጋለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 5:14

ስለዚህ ባል የሞተባቸው ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ፣ ልጆች እንዲወልዱ፣ ቤታቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ጠላትም የሚነቅፍባቸውን ነገር እንዳያገኝ እመክራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:27

በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ነውር የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳትና ከዓለም ርኩሰት ራስን መጠበቅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 12:42-44

አንዲት ምስኪን መበለት ግን ከአንድ ሳንቲም የማይበልጡ ሁለት የናስ ሳንቲሞች አስገባች። ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ይህች ድኻ መበለት ሙዳየ መባ ውስጥ ሌሎቹ ከጨመሩት የበለጠ አስገባች። እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን ከጕድለቷ ያላትን፣ መኖሪያዋን ሁሉ ሰጠች።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 7:12-15

ወደ ከተማዋ መግቢያ በር ሲደርስም፣ እነሆ፤ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው ከከተማዋ ወጡ፤ ሟቹም ለእናቱ አንድ ልጅ ብቻ ነበር፤ እናቱም መበለት ነበረች፤ ብዙ የከተማውም ሕዝብ ከርሷ ጋራ ነበረ። ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፣ “አይዞሽ፤ አታልቅሺ” አላት። ቀረብ ብሎም ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙትም ሰዎች ቀጥ ብለው ቆሙ፤ ኢየሱስም፣ “አንተ ጐበዝ፤ ተነሥ እልሃለሁ!” አለው። የሞተውም ሰው ቀና ብሎ ተቀመጠ፤ መናገርም ጀመረ። ኢየሱስም ወስዶ ለእናቱ ሰጣት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 18:1

ደቀ መዛሙርቱ ሳይታክቱ ሁልጊዜ መጸለይ እንደሚገባቸው ለማሳየት ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:7

ባሎች ሆይ፤ እናንተም ደግሞ ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ በኑሯችሁ ሁሉ ለሚስቶቻችሁ ዐስቡላቸው፤ ደካሞች ስለ ሆኑና የሕይወትንም በረከት ዐብረዋችሁ ስለሚወርሱ አክብሯቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 54:4

“አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 29:12

ለርዳታ የሚጮኸውን ችግረኛ፣ ድኻ አደጉንም ታድጌአለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 14:29

ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፣ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፣ አንተንም አምላክህ እግዚአብሔር በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 31:9

ተናገር፤ በጽድቅም ፍረድ፤ የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 82:3

ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ አደጎች ፍረዱላቸው፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 15:4

እግዚአብሔር፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል’ ብሎ ሲያዝዝ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 54:5

ባልሽ ፈጣሪሽ ነውና፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ታዳጊሽ የእስራኤል ቅዱስ ነው፤ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ነገሥት 4:1-7

የነቢያት ማኅበር ወገን ከሆነው የአንደኛው ሚስት፣ “አገልጋይህ ባሌ ሞቷል፤ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበር አንተ ታውቃለህ፤ አሁን ግን ባለዕዳ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ባሪያ አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቷል” ስትል ወደ ኤልሳዕ ጮኸች። ስለዚህ በሰገነቱ ላይ አንዲት ትንሽ ክፍል ቤት ሠርተን ዐልጋና ጠረጴዛ፣ ወንበርና ፋኖስ እናስገባለን፤ ከዚያም ወደ እኛ በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ማረፊያ ትሆነዋለች።” አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደዚያው መጥቶ ወደ ማረፊያ ክፍሉ በመውጣት ጋደም አለ። አገልጋዩን ግያዝንም፣ “ሱነማዪቱን ጥራት” አለው፤ በጠራትም ጊዜ መጥታ በፊቱ ቆመች። ኤልሳዕም፣ “ ‘ለእኛ ስትይ በጣም ተቸግረሻል፤ ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊአለሽ? ለንጉሡ ወይስ ለሰራዊቱ አዛዥ የምንነግርልሽ ጕዳይ አለን?’ ብለህ ጠይቃት” አለው። ሴቲቱም መልሳ፣ “እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው” አለችው። ኤልሳዕም፣ “ታዲያ ምን ይደረግላት” ሲል ጠየቀ። ግያዝም፣ “ልጅ እኮ የላትም፤ ባሏም ሸምግሏል” አለ። ኤልሳዕም፣ “በል እንግዲያው ጥራት” አለው፤ እርሱም ጠርቷት መጥታ በራፉ ላይ ቆመች። ኤልሳዕም፣ “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፣ “አይደለም ጌታዬ፣ አንተ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ ኋላ አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ!” አለችው። ሴትዮዋም ፀነሰች፤ ኤልሳዕ እንደ ነገራትም በተባለው ጊዜ ወንድ ልጅ ወለደች። ሕፃኑ አደገ፤ አንድ ቀንም አባቱ ከዐጫጆች ጋራ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። አባቱንም፣ “ራሴን! ራሴን!” አለው። አባቱም አገልጋዩን፣ “ተሸክመህ ወደ እናቱ አድርሰው” አለው። ኤልሳዕም፣ “ታዲያ እኔ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽ ምን እንዳለ ንገሪኝ” አላት። እርሷም፣ “አገልጋይህ ከጥቂት ዘይት በቀር በቤቷ ምንም ነገር የላትም” አለች። አገልጋዩም አንሥቶ እናቱ ዘንድ አደረሰው፤ ልጁም እስከ እኩለ ቀን ድረስ በእናቱ ጭን ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ሞተ። ወደ ላይ ወጥታም በእግዚአብሔር ሰው ዐልጋ ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች። ከዚያም ባሏን ጠርታ፣ “ወደ እግዚአብሔር ሰው በፍጥነት ደርሼ እንድመለስ አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝ” አለችው። ባሏም፣ “ዛሬ ወደ እርሱ መሄድ ለምን አስፈለገሽ? መባቻ ወይም ሰንበት አይደለም” አላት። እርሷም፣ “ምንም አይደል፤ ልሂድ” አለችው። ከዚያም አህያውን ጭና አገልጋይዋን፣ “ቶሎ ቶሎ ንዳ፤ እኔ ካልነገርኩህ በቀር ለእኔ ብለህ አታዝግም” አለችው። ስለዚህ ተነሥታ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደች። የእግዚአብሔር ሰው በሩቁ ሲያያት አገልጋዩን ግያዝን እንዲህ አለው፤ “ሱነማዪቱን አየሃት፤ ያቻትና! በል ሩጠህ ሂድና፣ ‘ምነው ደኅና አይደለሽምን? ባልሽ ደኅና አይደለምን? ልጅሽስ ደኅና አይደለምን?’ ብለህ ጠይቃት።” እርሷ፣ “ሁሉ ነገር ደኅና ነው” አለች። የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ተራራ ስትደርስም እግሩ ላይ ተጠመጠመች፤ ግያዝ ሊያስለቅቃት ሲመጣ፣ የእግዚአብሔር ሰው ግን፣ “እጅግ ዐዝናለችና ተዋት! እግዚአብሔር ይህን ለምን ከእኔ እንደ ሰወረውና እንዳልነገረኝ አልገባኝም” አለ። እርሷም፣ “ጌታዬ፤ ለመሆኑ እኔ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‘አጕል ተስፋ እንዳትሰጠኝ’ አላልሁህምን?” አለችው። ኤልሳዕም ግያዝን፣ “እንግዲህ ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬን ያዝና ሩጥ፤ መንገድ ላይ ሰው ብታገኝ ሰላም አትበል፤ ማንም ሰው ሰላም ቢልህ መልስ አትስጥ፤ በትሬንም በልጁ ፊት ላይ አድርግ” አለው። ኤልሳዕም እንዲህ አላት፤ “እንግዲያው ሂጂና ከጎረቤቶችሽ ሁሉ ጥቂት ሳይሆን ብዙ ማድጋ ተዋሺ፤ የልጁ እናት ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፤ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፣ ፈጽሞ ትቼህ አልሄድም” አለችው፤ ስለዚህ ተነሥቶ ተከተላት። ግያዝም ቀድሟቸው ሄዶ በትሩን በልጁ ፊት ላይ አደረገ፤ ነገር ግን ድምፅም፣ ምላሽም አልነበረም። ስለዚህ ግያዝ ወደ ኤልሳዕ ተመልሶ፣ “ልጁ አልነቃም” አለው። ኤልሳዕ ወደ ቤት ሲገባም ልጁ ሞቶ በዐልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። ወደ ውስጥም ገባ፤ ከዚያም በሩን በራሱና በልጁ ላይ ዘግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። በዐልጋው ላይ ወጥቶም በልጁ ላይ ተጋደመና አፉን በአፉ፣ ዐይኑን በዐይኑ፣ እጁን በእጁ ላይ አደረገ። ሙሉ በሙሉ እንደተዘረጋበትም፣ የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ። ኤልሳዕም ተነሥቶ በቤቱ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ከሄደ በኋላ ወደ ዐልጋው ወጥቶ እንደ ገና በልጁ ላይ ሙሉ ለሙሉ ተዘረጋበት፤ ልጁም ሰባት ጊዜ አስነጠሰውና ዐይኖቹን ከፈተ። ኤልሳዕም ግያዝን ጠርቶ፣ “ሱነማዪቱን ጥራት፤” አለው፤ እርሱም ጠራት። እንደ መጣችም፣ “በይ ልጅሽን ውሰጂ” አላት። እርሷም ገብታ በእግሩ ላይ ወደቀች፤ በምድርም ላይ ተደፋች፤ ልጇንም ይዛ ወጣች። ኤልሳዕ ወደ ጌልገላ ተመለሰ፤ በዚያም አገር ራብ ነበረ። የነቢያት ማኅበር በፊቱ ተቀምጠው ሳለ አገልጋዩን፣ “ትልቁን ምንቸት ጣድና ለእነዚህ ሰዎች ወጥ ሥራላቸው” አለው። ከእነርሱም አንዱ ቅጠላ ቅጠል ለማምጣት ወደ ሜዳ ወጥቶ፤ ዱር በቀል ሐረግ አገኘ፤ ከሐረጉም ላይ የቅል ፍሬ ለቅሞ በልብሱ ሙሉ ይዞ ተመለሰና ቈራርጦ በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን ማንም አላወቀም። ገብተሽም መዝጊያውን በአንቺና በልጆችሽ ላይ የኋሊት ዝጊው፤ ዘይቱንም በማድጋዎቹ ሁሉ ጨምሪ፤ እያንዳንዱ ማድጋ ሲሞላም ወደ አንድ በኩል አኑሪው።” ሰዎቹ እንዲመገቡትም ወጡ ወጣ፤ ገና አንደ ቀመሱትም፣ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ በምንቸቱ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም። ኤልሳዕም፣ “እስኪ ዱቄት አምጡልኝ” አለ። ያንም በምንቸቱ ውስጥ ጨምሮ፣ “እንዲመገቡት ለሰዎቹ አቅርቡላቸው” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ጕዳት የሚያስከትል ነገር አልተገኘም። አንድ ሰው ከበኵራቱ ፍሬ የተጋገረ ሃያ የገብስ ሙልሙልና ጥቂት የእሸት ዛላዎች በአቍማዳ ይዞ ከበኣልሻሊሻ ወደ እግዚአብሔር ሰው መጣ። ኤልሳዕም አገልጋዩን፣ “ሰዎቹ እንዲበሉት ስጣቸው” አለው። አገልጋዩም፣ “ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው አቀርባለሁ?” ሲል ጠየቀ። ኤልሳዕ ግን፣ “እንዲበሉት ለሰዎቹ ስጣቸው፤ እግዚአብሔር፣ ‘በልተው ይተርፋቸዋል’ ይላልና” አለው። ከዚያም አቀረበላቸው፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም በልተው ተረፋቸው። ስለዚህ ትታው ሄዳ መዝጊያውን በራሷና በልጆቿ ላይ የኋሊት ዘጋችው፤ ማድጎቹን እያቀረቡላትም እርሷ ትሞላ ጀመር። ማድጋዎቹ ሁሉ ከሞሉ በኋላ ልጇን፣ “ሌላ ማድጋ አምጣ” አለችው። እርሱ ግን፣ “ምንም የቀረ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም ዘይቱ መውረዱን አቆመ። እርሷም ሄዳ ይህንኑ ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው። እርሱም፣ “ሄደሽ ዘይቱን በመሸጥ ዕዳሽን ክፈይ፤ የተረፈውም ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ ይሁን” አላት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሩት 1:16-17

ሩት ግን እንዲህ አለች፤ “ተለይቼሽ እንድቀር ወይም እንድመለስ አትለማመጭኝ፤ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምትኖሪበትም እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል። በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ እዚያው እቀበራለሁ። ከእንግዲህ ሞት ከሚለየን በቀር ብለይሽ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ ከዚህም የከፋ ያድርግብኝ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሩት 2:10

በዚህ ጊዜ ወደ መሬት ዝቅ ብላ እጅ ነሣችው። እርሷም፣ “ባይተዋር የሆንሁትን እኔን ታስበኝ ዘንድ በፊትህ ሞገስ ለማግኘት የበቃሁት እንዴት ነው?” አለችው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 27:10

የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 5:3

ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:4

የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መጽናናትን ያገኛሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:13

ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:24

ቍጣዬ ይነሣል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የለሽ ይሆናሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 31:16-17

“ለድኻ የሚያስፈልገውን ከልክዬ ከሆነ፣ ወይም የመበለቲቱን ዐይን አፍዝዤ ከሆነ፣ እንጀራዬን ከድኻ አደጉ ጋራ ሳልካፈል፣ ለብቻዬ በልቼ ከሆነ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 94:6

መበለቲቱንና መጻተኛውን ገደሉ፤ የድኻ አደጉንም ነፍስ አጠፉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:21-22

ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፤ ከዐመፀኞችም ጋራ አትተባበር፤ ሁለቱም የሚያመጡት መዓት፤ ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 18:7-8

እግዚአብሔርስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? ከመጠን በላይስ ችላ ይላቸዋልን? እላችኋለሁ፤ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ እምነትን ያገኝ ይሆንን?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 25:35-36

ምክንያቱም ተርቤ አብልታችሁኛል፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛል፤ ታርዤ አልብሳችሁኛል፤ ታምሜ አስታምማችሁኛል፤ ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 112:9

በልግስና ለድኾች ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 9:18

ድኾችን ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤ የችግረኞችንም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 29:13

በሞት አፋፍ ላይ የነበረ መርቆኛል፤ የመበለቲቱንም ልብ አሳርፌአለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 4:10

አንዱ ቢወድቅ፣ ባልንጀራው ደግፎ ያነሣዋል። ቢወድቅ የሚያነሣው ረዳት የሌለው ግን፣ እንዴት አሳዛኝ ነው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:22-24

“ባል በሞተባት ወይም አባትና እናት በሌለው ልጅ ላይ ግፍ አትዋሉ። ግፍ ብትውሉባቸውና ወደ እኔ ቢጮኹ፣ ጩኸታቸውን በርግጥ እሰማለሁ። ቍጣዬ ይነሣል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለቶች፣ ልጆቻችሁም አባት የለሽ ይሆናሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:25

ጕልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ፤ ነገር ግን ጻድቅ ሲጣል፣ ዘሩም እንጀራ ሲለምን አላየሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 139:17-18

አምላክ ሆይ፤ ለእኔ ያለህ ሐሳብ እንዴት ክቡር ነው! ቍጥሩስ ምንኛ ብዙ ነው! ልቍጠራቸው ብል፣ ከአሸዋ ይልቅ ይበዙ ነበር። ተኛሁም ነቃሁም፣ ገና ከአንተው ጋራ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:23

ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጕቦን ይወድዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 22:3

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ከጨቋኙ እጅ አድኑት፤ መጻተኛውን፣ ወላጅ የሌለውንና መበለቲቱን አትበድሉ፤ አትግፏቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 20:47

በረዥም ጸሎታቸው እያሳበቡ የመበለቶችን ቤት ያራቍታሉ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:7

ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 2:15-16

አንድ ወንድም ወይም አንዲት እኅት የሚለብሱት ልብስም ሆነ የሚመገቡት ምግብ ዐጥተው፣ ከእናንተ መካከል አንዱ፣ “በሰላም ሂዱ፤ አይብረዳችሁ፤ ጥገቡ” ቢላቸው፣ ለሰውነታቸው ግን የሚያስፈልጋቸውን ባይሰጣቸው፣ ምን ይጠቅማቸዋል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:2

አንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህም ሁኔታ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 68:6

እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተ ሰብ መካከል ያኖራል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃል፤ ዐመፀኞች ግን ምድረ በዳ ይኖራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:10

በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 15:1

እኛ ብርቱዎች የሆንን፣ የደካሞችን ጕድለት መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:1-2

እርስ በርሳችሁ እንደ ወንድማማች ተዋደዱ። በድንኳኒቱም የሚያገለግሉ ከዚያ ሊበሉ መብት ያላገኙበት መሠዊያ አለን። ሊቀ ካህናቱ ስለ ኀጢአት ስርየት የሚሆነውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ ሥጋ ግን ከሰፈር ውጭ ይቃጠላል። እንዲሁም ኢየሱስ በራሱ ደም አማካይነት ሕዝቡን ሊቀድስ ከከተማው በር ውጭ መከራን ተቀበለ። ስለዚህ እኛም እርሱ የተሸከመውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደ እርሱ እንውጣ። ምክንያቱም በዚህ ቋሚ ከተማ የለንም፤ ነገር ግን ወደ ፊት የምትመጣዋን ከተማ እንጠብቃለን። ስለዚህ ዘወትር የምስጋናን መሥዋዕት፣ ይኸውም ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በኢየሱስ አማካይነት ለእግዚአብሔር እናቅርብ። ደግሞም መልካም ማድረግንና ያላችሁንም ከሌሎች ጋራ መካፈልን አትርሱ፤ እግዚአብሔር ደስ የሚሠኘው እንደዚህ ባለው መሥዋዕት ነውና። ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጕዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው፤ አለዚያ አይበጃችሁም። ለእኛ ደግሞ ጸልዩልን። በሁሉም መንገድ በመልካም አኗኗር ለመኖር የሚናፍቅ ንጹሕ ኅሊና እንዳለን ርግጠኞች ነን። በተለይም ወደ እናንተ በፍጥነት ተመልሼ እንድመጣ ትጸልዩልኝ ዘንድ ዐደራ እላችኋለሁ። እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ፣ ሳያውቁ መላእክትን አስተናግደዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 113:7-8

ድኻውን ከዐፈር ያነሣል፤ ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤ ከሕዝቡም ሹማምት ጋራ ያስቀምጠዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 6:29-30

ከሕዝብህ ማንኛውም ሰው ወይም መላው እስራኤል ጭንቀቱንና ሕመሙን ዐውቆ እጆቹን ወደዚህ ቤት በመዘርጋት ማንኛውንም ጸሎትና ልመና በሚያቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ መላው የእስራኤል ጉባኤ በዚያ ቆሞ ሳለ፣ ንጉሡ ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ ጉባኤውን ባረከ። በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ይቅር በል፤ አድርግም። የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ የምታውቅ አንተ ብቻ ስለ ሆንህ ልቡን ለምታውቀው ለእያንዳንዱ ሰው እንደ አካሄዱ ክፈለው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:65-67

ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ጠጅ ስካር እንደ በረደለት ጀግናም ብድግ አለ። ጠላቶቹን መትቶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤ የዘላለም ውርደትም አከናነባቸው። የዮሴፍን ድንኳን ተዋት፤ የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 20:1-2

እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤ የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ። ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ፤ ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 72:12

ድኻው በጮኸ ጊዜ፣ ችግረኛውና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 10:1-2

ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ ጭቈና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ ወዮላቸው! የጣዖታትን መንግሥታት፣ ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ መንግሥታት የሚበልጡትን እጄ እንደ ያዘች ሁሉ፣ በሰማርያና በጣዖቶቿ ያደረግሁትን፣ በኢየሩሳሌምና በተቀረጹ ምስሎቿስ እንዲሁ አላደርግምን?” ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣ እንዲህ ይላል፤ “የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፤ “ ‘ይህን ሁሉ ያደረግሁት በክንዴ ብርታት ነው፤ ደግሞም በጥበቤ አስተዋይ ነኝና። የመንግሥታትን ድንበር አፈረስሁ፤ ሀብታቸውን ዘረፍሁ፤ ነገሥታታቸውን እንደ አንድ ኀያል ሆኜ አዋረድሁ። ሰው እጁን ወደ ወፍ ጐጆ እንደሚሰድድ፣ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቍላል እንደሚሰበስቡ፣ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’ ” መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው። ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል። የእስራኤል ብርሃን እሳት፣ ቅዱሱም ነበልባል ይሆናል፤ በአንድ ቀንም እሾኹንና ኵርንችቱን እሳት ይበላዋል፤ ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፣ የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፣ ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል። በደኑ ውስጥ የሚተርፉት ዛፎች በጣም ጥቂት ናቸው፤ ሕፃን ልጅ እንኳ ቈጥሮ ሊመዘግባቸው ይችላል። የድኾችን መብት ለሚገፍፉ፣ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 68:4

ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም ተቀኙ፤ በደመናት ላይ የሚሄደውን ከፍ አድርጉት፤ ስሙ እግዚአብሔር በተባለው ፊት፣ እጅግ ደስ ይበላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:76

ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል መሠረት፣ ምሕረትህ ለመጽናናት ትሁነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 16:11

አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችህ፣ በከተሞችህ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፣ በመካከልህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች አምላክህ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:24-25

እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች። ይህች ባሕር ሰፊና የተንጣለለች ናት፤ ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ ስፍር ቍጥር የሌላቸውም የሚርመሰመሱ ፍጥረታት በውስጧ አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 31:24-25

“ወርቅን ተስፋ አድርጌ፣ ወይም ንጹሑን ወርቅ፣ ‘አንተ መታመኛዬ ነህ’ ብዬ ከሆነ፣ እጄ ባገኘችው ሀብት፣ በባለጠግነቴም ብዛት ደስ ብሎኝ ከሆነ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 23:22

የወለደህን አባትህን አድምጥ፤ እናትህንም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:28

እግዚአብሔር ፍትሕን ይወድዳልና፣ ታማኞቹንም አይጥልም። ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፤ የኀጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 61:1

የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 146:7

ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 19:29

ስለ ስሜ ብሎ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን ወይም ዕርሻን የሚተው ሁሉ መቶ ዕጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 14:6

እናንተ የድኾችን ዕቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን መጠጊያቸው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:82

“መቼ ታጽናናኛለህ?” እያልሁ፣ ዐይኖቼ ቃልህን በመጠባበቅ ደከሙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 3:1

ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 38:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ። ልቤ በኀይል ይመታል፤ ጕልበት ከድቶኛል፤ የዐይኔም ብርሃን ጠፍቷል። ከቍስሌ የተነሣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ፤ ጎረቤቶቼም ርቀው ቆሙ። ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ሊያጠፉኝ ዛቱ፤ ቀኑንም ሙሉ ተንኰል ይሸርባሉ። እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቈሮ፣ አፉንም መክፈት እንደማይችል ዲዳ ሆንሁ። በርግጥም ጆሮው እንደማይሰማ፣ አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በተስፋ እጠብቅሃለሁ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ፤ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ። እኔ፣ “ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ አይበላቸው፤ እግሬም ሲንሸራተት፣ በላዬ አይኵራሩብኝ” ብያለሁና። ልወድቅ ተቃርቤአለሁ፤ ከሥቃዬም ከቶ አልተላቀቅሁም። በደሌን እናዘዛለሁ፤ ኀጢአቴም አውካኛለች። ብርቱዎች ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤ ያለ ምክንያት የሚጠሉኝም ስፍር ቍጥር የላቸውም። ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና፤ እጅህም ተጭናኛለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:89

እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃልህ በሰማይ፣ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 10:12

በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ልዩነት የለም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፤ የሚለምኑትንም አብዝቶ ይባርካል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:12

የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:19

እርሱ አስቀድሞ ወድዶናልና እኛ እንወድደዋለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 91:1-2

በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል። ክፉ ነገር አያገኝህም፤ መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይሰናከል፤ በእጆቻቸው ያነሡህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል። በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ። “ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ። ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ። ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።” እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 1:3-4

የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 49:15

“እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:22-23

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው። እንደነዚህ ያሉትንም የሚከለክል ሕግ የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 31:20

ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣ እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 3:22-23

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህም ብዙ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:7

“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 11:28

“እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 113:9

መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል። ሃሌ ሉያ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:5-6

ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ የቀድሞ ቅዱሳን ሴቶች ራሳቸውን ያስዋቡት በዚህ ዐይነት ለባሎቻቸው በመገዛት ነበርና። ሣራም አብርሃምን “ጌታዬ” እያለች ትታዘዘው ነበር፤ እናንተም ምንም ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚኦ አልፋና ኦሜጋ ነህ! የሰማይና የምድር ፈጣሪ አባት ሆይ፥ አንተ የመጀመሪያውና የመጨረሻው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው ነህ። አባት ሆይ፥ በኢየሱስ ስም፥ በአንተ ለማያምኑት ነፍሳት መዳን እጸልያለሁ። መንፈስ ቅዱስህ እንዲገስጻቸውና ቃልህን እንዲያነቡ፥ ፊትህን እንዲፈልጉ እና በኃይልህ እንዲለወጡ እንዲያሳስባቸው እለምንሃለሁ። የተወደድክ አምላክ ሆይ፥ ልባቸውን በሙሉ ለአንተ እንዲገዙ ግረዝ። በቃልህ "እግዚአብሔር አምላክህም ልብህን የዘርህንም ልብ ይገርዛል፥ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እግዚአብሔር አምላክህን ትወድድ ዘንድ፥ በሕይወትም ትኖር ዘንድ።" ይላል። የምሕረት አምላክ ሆይ፥ ለእነርሱ የስጋ ልብ፥ ሕያውና ለእግዚአብሔር የሚሰማ ልብ ስጣቸው፤ የድንጋይ ልብን ከእነርሱ አርቅ። መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ በማያምኑት ላይ ሥራና ልባቸውን አንጻ። "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም" ብለሃልና እግዚአብሔር ኢየሱስ ሆይ፥ መንፈስህን በእነርሱ ውስጥ እንድታኖር እንጸልያለን፥ ወደ ፊትህ ሳባቸው። አምላክ ሆይ፥ ነፍሳቸው በዘላለም እሳት እንዳትጠፋ፥ ምሕረት አድርግላቸውና ንስሐ እንዲገቡ አድርግ። በኢየሱስ ስም፤ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች