እግዚአብሔርን ለማስደሰት ሙዚቃ እንደተፈጠረ ታውቃለህ? እርሱ ለእኛ የመግለፅ ፀጋ ቢሰጠንም፣ የሁሉም ነገር ምንጭ የእርሱ ታላቅ የፍጥረት ኃይል ነው።
በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ፣ ሙዚቃ ለተለያዩ አጋጣሚዎች እንዴት እንደሚውል እናያለን። የእግዚአብሔርን ስም ለማምለክና ታላቅነቱን ለማወደስ፣ በፊቱ ለመደነስ፣ በመከራ ጊዜ ሰላም ለማግኘት፣ የጠላቶችን ሽንፈት ለማወጅና ድልን ለመዘመር ሙዚቃ ይውል ነበር።
ብዙዎቹ መዝሙራት እንደ ዘፈን ተጽፈው ነበር። አንዳንዶቹ እንደ ጠላቶች ላይ ድል (ዘፀአት 15:1-18፤ መሳፍንት 5:1-31) ካሉ ተጨባጭ ክስተቶች ጋር የተያያዙ ናቸው። ሌሎች ደግሞ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ የእርዳታ ልመና ወይም መሪነትን ይገልፃሉ።
መላእክት የኢየሱስን ልደት ሲያበስሩ እንኳን ዘምረዋል (ሉቃስ 2:13-14)።
ዲያብሎስ የሙዚቃን ትክክለኛ አላማ ለማበላሸት፣ ዝሙትንና ርኩሰትን ለማስፋፋት እንደሚሞክር እናውቃለን። ስለዚህ፣ የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን መጠን የሙዚቃን መነሻ መጠበቅና ከዚህ ዓለም ስርዓት መከላከል አለብን። ይህ ስርዓት በዘላለማዊው የተፈጠረ አይደለምና።
በመዝሙርና በውዳሴ፣ በመንፈሳዊም ዝማሬ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ በልባችሁ ለጌታ ተቀኙ፤ አዚሙም። ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ። በዚህም እግዚአብሔር አብን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር ሁልጊዜ አመስግኑ።
ከዚያም ሙሴና እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ “ከፍ ከፍ ብሎ ከብሯልና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሏልና። አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤ ባሕርም ከደናቸው፤ በኀያላን ውሆች፣ እንደ ብረት ሰጠሙ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአማልክት መካከል፣ እንደ አንተ ማን አለ? በቅድስናው የከበረ፣ በክብሩ የሚያስፈራ፣ ድንቆችን የሚያደርግ፣ እንደ አንተ ማን አለ? “ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው። በማይለወጠው ፍቅርህ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህን ትመራለህ፤ እነርሱን በብርታትህ፣ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ትመራቸዋለህ። አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤ የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል። የኤዶምም አለቆች ይርዳሉ፤ የሞዓብ አለቆች በእንቅጥቃጤ ይያዛሉ፤ የከነዓን ሕዝብ ይቀልጣሉ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህ እስከሚያልፉ ድረስ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ በክንድህ ብርታት፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ማደሪያህ እንዲሆን በሠራኸው ስፍራ፣ ጌታ ሆይ፤ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ፣ ታመጣቸዋለህ፤ ትተክላቸዋለህም። “እግዚአብሔር፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።” የፈርዖን ፈረሶች፣ ሠረገሎቹና ፈረሰኞቹ ወደ ባሕሩ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሃ በላያቸው ላይ መለሰባቸው፤ እስራኤላውያን ግን በባሕሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ተሻገሩ። “እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤ በድነታችንም ዐለት እልል እንበል። ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤ እኔም፣ “በልቡ የሳተ ሕዝብ ነው፤ መንገዴንም አላወቀም” አልሁ። ስለዚህ እንዲህ ብዬ በቍጣዬ ማልሁ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም።” ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤ በዝማሬም እናወድሰው።
ክፉው መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሳኦል ላይ በሚመጣበት ጊዜ፣ ዳዊት በገናውን ይዞ ይደረድር ነበር፤ ሳኦልም ይሻለው ነበር፤ ክፉውም መንፈስ ከርሱ ይርቅ ነበር።
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሆነው በቅኔና በበገና፣ በመሰንቆና በከበሮ፣ በጸናጽልና በመለከት በሙሉ ኀይላቸው በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።
የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
ዳዊትም በዜማ መሣሪያ፣ ማለትም በመሰንቆ፣ በበገናና በጸናጽል እየታጀቡ የደስታ ዜማዎችን የሚያዜሙ መዘምራንን ከወንድሞቻቸው መካከል እንዲሾሙ ለሌዋውያኑ መሪዎች ነገራቸው።
እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት። ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርጋለች፤ እርሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው። ልባችን በርሱ ደስ ይለዋል፤ በቅዱስ ስሙ ታምነናልና። እግዚአብሔር ሆይ፤ ተስፋ ባደረግንህ፣ በእኛ ላይ ምሕረትህ ትሁን። አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤ በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ።
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ። ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤ ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ። እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴውም ብዙ ነው፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል።
መለከት ነፊዎችና ዘማሪዎችም በአንድነት አንድ ድምፅ ሆነው ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና አቀረቡ፤ በመለከት፣ በጸናጽልና በሌሎች መሣሪያዎች ታጅበውም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔርን እያወደሱ፣ “እርሱ ቸር ነው፣ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉ ዘመሩ። ከዚያም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በደመና ተሞላ።
የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ሌዋውያኑ በምስጋና መዝሙር፣ በጸናጽል፣ በበገናና በመሰንቆ ድምፅ የምረቃውን በዓል በደስታ እንዲያከብሩ ከሚኖሩበት ተፈልገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ንጉሥ ሕዝቅያስና ሹማምቱ፣ ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለራእዩ በአሳፍ ቃል እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። እነርሱም ውዳሴውን በደስታ ዘመሩ፤ ራሳቸውንም አጐንብሰው ሰገዱ።
ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት አከናወኑ። የበላይ ሆነው አመራር የሚሰጧቸውም ከሜራሪ ጐሣ የሆኑት ሌዋውያን፣ ኢኤትና አብድዩ፣ ከቀዓት ጐሣ ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። በዜማ ዕቃ የላቀ ችሎታ የነበራቸው ሌዋውያን ሁሉ፣
በውዳሴና በምስጋናም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲሉ ዘመሩ፤ “ቸር ነውና፤ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።” የእግዚአብሔር ቤት መሠረት ስለ ተጣለ፣ ሕዝቡ ሁሉ በታላቅ ድምፅ እልል እያሉ፣ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረቡ።
አምላክ ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ እቀኛለሁ፤ በፍጹም ነፍሴም እዘምራለሁ። ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? ወደ ኤዶምያስ ማን ይመራኛል? እግዚአብሔር ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋራ አትወጣም። በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤ የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና። በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና። በገናና መሰንቆም ተነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ። ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ።
ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅኖች ሊወድሱት ይገባቸዋል። እግዚአብሔር የሕዝቦችን ምክክር ከንቱ ያደርጋል፤ የሕዝብንም ዕቅድ ያጨናግፋል። የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን ለዘላለም ይጸናል፤ የልቡም ሐሳብ ለትውልድ ሁሉ ነው። ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነው ሕዝብ፣ ለርስቱ የመረጠውም ወገን፤ እግዚአብሔር ከሰማይ ይመለከታል፤ የሰውንም ልጆች ሁሉ ያያል፤ ከማደሪያው ቦታ ሆኖ፣ በምድር ወደሚኖሩት ሁሉ ይመለከታል፤ እርሱ የሁሉን ልብ የሠራ፣ የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያስተውል ነው። ንጉሥ በሰራዊቱ ታላቅነት አይድንም፤ ጀግናም በኀይሉ ብርታት አያመልጥም። በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤ በብርቱ ጕልበቱም ማንንም አያድንም። እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ ምሕረቱንም በሚጠባበቁት ላይ አትኵረዋል። በዚህም ነፍሳቸውን ከሞት ያድናል፤ በራብ ዘመንም በሕይወት ያኖራቸዋል። እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት። ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርጋለች፤ እርሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው። ልባችን በርሱ ደስ ይለዋል፤ በቅዱስ ስሙ ታምነናልና። እግዚአብሔር ሆይ፤ ተስፋ ባደረግንህ፣ በእኛ ላይ ምሕረትህ ትሁን። አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤ በገናውን ባማረ ቅኝት ደርድሩ፤ እልልም በሉ።
ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች፣ እነዚህን ነገሮች አስታወስሁኝ፤ ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ፣ በእልልታና በምስጋና መዝሙር፣ በአእላፍ ሕዝብ መካከል፣ እንዴት ከሕዝቡ ጋራ እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ።
ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ፤ ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ። ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ፣ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ አፍህን በሰፊው ክፈተው፤ እኔም እሞላዋለሁ። “ሕዝቤ ግን አላደመጠኝም፤ እስራኤልም እጅ አልሰጥ አለኝ። ስለዚህ በገዛ ዕቅዳቸው እንዲሄዱ፣ አሳልፌ ለደንዳናው ልባቸው ሰጠኋቸው። “ምነው ሕዝቤ ቢያደምጠኝ ኖሮ፣ እስራኤል በመንገዴ በሄደ ኖሮ፣ ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባንበረከክኋቸው ነበር፤ እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ ባነሣሁ ነበር። እግዚአብሔርን የሚጠሉ በፊቱ ይርዳሉ፤ ቅጣታቸውም እስከ ዘላለም የሚዘልቅ ነው። እናንተን ግን ምርጡን ስንዴ አበላችኋለሁ፤ ከዐለቱም ማር አጠግባችኋለሁ።” ዝማሬውን ጀምሩ፤ ከበሮውን ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ጥዑም ዜማ አሰሙ።
እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤ የእኔን ቀንድ ግን እንደ አውራሪስ ቀንድ ከፍ ከፍ አደረግኸው፤ በለጋ ዘይትም አረሰረስኸኝ። ዐይኖቼ የባላንጦቼን ውድቀት አዩ፤ ጆሮዎቼም የክፉ ጠላቶቼን ድቀት ሰሙ። ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ። በእግዚአብሔር ቤት ተተክለዋል፤ በአምላካችንም አደባባይ ይንሰራፋሉ። ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ፤ እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ። “እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤ እርሱ ዐለቴ ነው፤ በርሱ ዘንድ እንከን የለም” ይላሉ። ምሕረትህን በማለዳ፣ ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤ ዐሥር አውታር ባለው በገና፣ በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው።
ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤ ምድር ሁሉ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ነገሠ” በሉ፤ ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም፤ እርሱ ለሕዝቦች በእኩልነት ይፈርዳል። ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤ መስኩና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ፤ ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፤ እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይፈርዳል። ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤ ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ።
መለከት ነፊዎችና ዘማሪዎችም በአንድነት አንድ ድምፅ ሆነው ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና አቀረቡ፤ በመለከት፣ በጸናጽልና በሌሎች መሣሪያዎች ታጅበውም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔርን እያወደሱ፣ “እርሱ ቸር ነው፣ ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” እያሉ ዘመሩ። ከዚያም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በደመና ተሞላ። የእግዚአብሔር ክብር የአምላክን ቤተ መቅደስ ሞልቶት ስለ ነበር፣ ከደመናው የተነሣ ካህናቱ አገልግሎታቸውን ማከናወን አልቻሉም።
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤ ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤ በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤ በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣ በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።
ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ፤ ማቄን አውልቀህ ፍሥሓን አለበስኸኝ፤ እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።
ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ። እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤ ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው። ሃሌ ሉያ። በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ። እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ። ስሙን በሽብሸባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት።
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በታላቅ ጠፈሩ አመስግኑት። ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤ እጅግ ታላቅ ነውና አመስግኑት። በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ ወድሱት። በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ በባለአውታር መሣሪያና በእንቢልታ አመስግኑት። ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤ ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት። እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።
እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።
እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
እግዚአብሔር ጽዮንን በርግጥ ያጽናናታል፤ ፍርስራሾቿንም በርኅራኄ ይመለከታል፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔድን፣ በረሓዋንም እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፤ ተድላና ደስታ፣ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ በርሷ ይገኛሉ።
ስሚ! ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገዋል፤ በአንድነት በእልልታ ይዘምራሉ። እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ፣ በዐይኖቻቸው ያያሉ። እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቷል፤ ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷልና።
መጥተውም በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በእግዚአብሔርም ልግስና፣ በእህሉ፣ በወይን ጭማቂውና በዘይቱ፣ በፍየልና በበግ ጠቦት፣ በወይፈንና በጊደር ደስ ይሰኛሉ፤ ውሃ እንደማይቋረጥባት የአትክልት ስፍራ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህም አያዝኑም። ኰረዶች ይዘፍናሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤ ጐረምሶችና ሽማግሌዎችም ይፈነጥዛሉ፤ ልቅሷቸውን ወደ ደስታ እለውጣለሁ፤ ከሐዘናቸውም አጽናናቸዋለሁ፤ ደስታንም እሰጣቸዋለሁ።
እንዲሁም አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ ያመሰግኑት ዘንድ ነው፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ።”
መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፣ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችም በበጉ ፊት በግንባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም የቅዱሳን ጸሎት የሆኑትን በገናና ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሙዳይ ይዘው ነበር። እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።
ከሰማይ እንደ ብዙ ውሃ ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የሰማሁት ድምፅ በገና ደርዳሪዎች እንደሚደረድሩት ዐይነት ነበረ። ወይኑም ከከተማው ውጭ በወይን መጭመቂያ ውስጥ ተረገጠ፤ ከፍታው እስከ ፈረስ ልጓም የሚደርስ፣ ርዝመቱ ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ያህል ደም ከመጭመቂያው ወጣ። እነርሱም በዙፋኑ ፊት፣ በአራቱ ሕያዋን ፍጡራንና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ መዝሙር ዘመሩ። ከምድር ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺሕ ሰዎች በቀር መዝሙሩን ማንም ሊማረው አልቻለም።
ከእሳት ጋራ የተቀላቀለ የብርጭቆ ባሕር የሚመስል አየሁ፤ በባሕሩም አጠገብ አውሬውን፣ ምስሉንና የስሙን ቍጥር ድል የነሡትን ቆመው አየሁ፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን በገና ይዘው፣ የእግዚአብሔር ባሪያ የሆነውን የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፤ “ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው። የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ፤ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።