Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 97 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነው

1 እግዚአብሔር ንጉሥ ነው! ምድር ሆይ ደስ ይበልሽ! እናንተ በባሕር ውስጥ ያላችሁ ደሴቶች ሁሉ፥ ደስ ይበላችሁ!

2 ብሩህና ጥቊር ደመና ዙሪያውን ከበውታል፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።

3 እሳት እፊት እፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ያቃጥላል።

4 መብረቁ በዓለም ላይ ያበራል፤ ምድርም አይታ ትንቀጠቀጣለች።

5 በምድር ሁሉ ጌታ በእግዚአብሔር ፊት፥ ተራራዎች እንደ ሰም ይቀልጣሉ።

6 ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፤ ሕዝቦች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።

7 ለጣዖቶች የሚሰግዱና በእነርሱ የሚመኩ ሁሉ ያፍራሉ፤ እናንተ ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ ለእግዚአብሔር ስገዱ።

8 አምላክ ሆይ! ስለ ትክክለኛ ፍርድህ የጽዮን ሕዝብ ደስ ይላቸዋል፤ የይሁዳ ከተሞችም ሐሤት ያደርጋሉ።

9 እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል አምላክ ነህ፤ ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በሥልጣንህ ሥር ናቸው።

10 እግዚአብሔር ክፉ ነገርን የሚጠሉትን ሁሉ ይወዳል፤ ታማኞች አገልጋዮቹን ያድናቸዋል፤ ከክፉ መንፈስ ኀይልም እንዲያመልጡ ያደርጋቸዋል።

11 ብርሃን ለደጋግ ሰዎች፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ይወጣላቸዋል።

12 እግዚአብሔር ስላደረገው ነገር ጻድቃን ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ!

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች