Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማሕልየ መሓልይ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ በም​ድረ በዳ ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልጅ ወን​ድ​ሜን ያገ​ኛ​ች​ሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍ​ቅር የተ​ነሣ መታ​መ​ሜን ትነ​ግ​ሩት ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እማጠናችኋለሁ፤ ውዴን ካገኛችሁት፣ ምን ትሉት መሰላችሁ? በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አስምላችኋለሁ፥ ውዴን ያገኛችሁት እንደሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ እኔ ከፍቅሩ የተነሣ መታመሜን እንድትነግሩት ዐደራ እላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አምላችኋለሁ፥ ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማሕልየ መሓልይ 5:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድን​ኳ​ኖች እንደ ሰሎ​ሞ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች።


በሽቱ አጸ​ኑኝ፥ በእ​ን​ኮ​ይም አበ​ረ​ታ​ቱኝ፥ በፍ​ቅሩ ተነ​ድ​ፌ​አ​ለ​ሁና።


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ፥ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት፥ በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽናት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት፥ በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ወን​ድ​ሞች፥ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ስለ እኔ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ትተጉ ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ፍቅር እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች