ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 45:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በክብር ሦስተኛ ነው፤ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀንቶአልና፥ ሕዝቡንም ለማስተማር አስነሥቶታልና፥ በልቡናው ቸርነትም ከእግዚአብሔር ፈቃድ የተነሣ ለእስራኤል አስተሰረየ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ጌታን በመፍራት ትጋቱ፥ ሕዝቡ ባመፀ ወቅት በእምነቱ በመጽናቱ፥ በልበ ሙሉነትና በድፍረት በመቆሙ፥ ለእሥራኤልም ስርየትን በማስገኘቱ፥ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ ክብርን በተመለከተ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |