Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሩት 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፥ በእርጅናሽም ይመግብሻል አሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ልጁ ሕይወትሽን ያድሳታል፤ በእርጅና ዘመንሽም ይጦርሻል፤ የምትወድድሽና ከሰባት ወንዶች ልጆች የምትበልጥብሽ ምራትሽ ወልዳዋለችና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፤ በእርጅናሽም ይመገባሻል፤” አሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሩት 4:15
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያም አን​ተና የቤ​ትህ ሰዎች የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ እን​ዳ​ት​ቸ​ገሩ እመ​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አም​ስት ዓመት ቀር​ቶ​አ​ልና፤


ዮሴ​ፍም ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ ለአ​ባ​ቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው እየ​ሰ​ፈረ እህ​ልን ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ቸው ነበር።


እስከ ሽም​ግ​ልና ድረስ እኔ ነኝ፤ እስከ ሽበ​ትም ድረስ እኔ ነኝ፤ እኔ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ሠር​ቻ​ለሁ፤ እኔም ይቅር እላ​ለሁ፤ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ።


ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፥ ሞግዚትም ሆነችው።


ባልዋ ሕል​ቃ​ናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ እነ​ሆኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ለምን ታለ​ቅ​ሻ​ለሽ? ለም​ንስ አት​በ​ዪም? ለም​ንስ ልብሽ ያዝ​ን​ብ​ሻል? እኔስ ከዐ​ሥር ልጆች አል​ሻ​ል​ሽ​ምን?” አላት።


እን​ጀራ ጠግ​በው የነ​በሩ ተራቡ፤ ተር​በ​ውም የነ​በሩ ጠገቡ፤ መካ​ኒቱ ሰባት ወል​ዳ​ለ​ችና፥ ብዙም የወ​ለ​ደ​ችው መው​ለድ አል​ቻ​ለ​ችም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች