ራእይ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እንግዲህ የተቀበልኸውንና የሰማኸውን አስታውስ፤ ታዘዘውም፤ ንስሓም ግባ። ባትነቃ ግን እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በየትኛው ሰዓት እንደምመጣብህም አታውቅም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እንግዲህ ቃሉን እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። ባትነቃ ግን እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንደምመጣብህ ከቶ አታውቅም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እንግዲህ ምን ዐይነት ትምህርት እንደ ተቀበልክና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ፤ ባትነቃ ግን እንደ ሌባ በድንገት እመጣብሃለሁ፤ በምን ሰዓት ወደ አንተ እንደምመጣ አታውቅም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም። ምዕራፉን ተመልከት |