Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 89:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሺህ ዓመት በፊ​ትህ እን​ዳ​ለ​ፈች እንደ ትና​ንት ቀን፥ እንደ ሌሊ​ትም ሰዓት ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤ ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ፥ ለአገልጋዬም ለዳዊት ማልሁ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሰጠኸውም የተስፋ ቃል “ዘርህ ለዘለዓለም ይነግሣል፤ ትውልድህንም ለዘለዓለም አጸናዋለሁ” የሚል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 89:4
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንተ ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና አሁን እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊ​ትህ ይሆን ዘንድ የባ​ሪ​ያ​ህን ቤት እባ​ክህ ባርክ፤ በበ​ረ​ከ​ት​ህም የባ​ሪ​ያህ ቤት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ረክ።”


እኔ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የሚ​ገዛ ሰውን ከአ​ንተ አላ​ጠ​ፋም ብዬ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት እንደ ተና​ገ​ርሁ፥ የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህን ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።


እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ልጅም ይሆ​ነ​ኛል፤ እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ቱ​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአ​ባቴ ቤት ሁሉ መር​ጦ​ኛል፤ ይሁ​ዳ​ንም አለቃ ይሆን ዘንድ መር​ጦ​ታል፤ ከይ​ሁ​ዳም ቤት የአ​ባ​ቴን ቤት መር​ጦ​አል፤ ከአ​ባ​ቴም ልጆች መካ​ከል በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ያነ​ግ​ሠኝ ዘንድ እኔን ሊመ​ር​ጠኝ ወደደ።


ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ውን አውቅ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እስ​ክ​ገባ ድረስ፥


አቤቱ፥ አንተ ለልጅ ልጅ ሁሉ መጠ​ጊያ ሆን​ህ​ልን።


እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።


በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፣ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፣ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።


ኢሳ​ይ​ያ​ስም ደግሞ እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “የእ​ሴይ ዘር ይነ​ሣል፤ ከእ​ርሱ የሚ​ነ​ሣ​ውም ለአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ሕዝ​ቡም ተስፋ ያደ​ር​ጉ​ታል።”


“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች