መዝሙር 89:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ ያቃናልናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤ በሞገስህም ቀንዳችንን ከፍ ከፍ አደረግህ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በስምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል፥ በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ፥ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ገናናው ኀይልህ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ በቸርነትህም ብርታታቸው እያደገ ይሄዳል። ምዕራፉን ተመልከት |
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ያደክማቸዋል፤ እግዚአብሔር ብቻ ቅዱስ ነው፤ ጥበበኛ በጥበቡ አይመካ፤ ኀይለኛም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይመካ፤ የሚመካ ግን በዚህ ይመካ፤ እግዚአብሔርን በማወቅና በማስተዋል፤ በምድርም መካከል ፍርድንና እውነትን በማድረግ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ወጣ፤ አንጐደጐደም። ጻድቅ እርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሦቻችንም ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”